ላለፉት ግማሽ ምዕተ ዓመታት የገነባናቸው ከተሞች የሚያቀራርቡን ሳይሆኑ እርስ በርሳችን የሚያራርቁን ናቸው።

​የሰው ልጅ  "የከተማ መስፋፋት" (Urban Sprawl)    ተጽእኖ ስር ወድቆ የተሸነፈ  ይመስላል። ይህም መስፋፋት   በመኪና ላይ ጥገኛ የሆነና የተበታተነ መልክዓ ምድር ሲሆን፣ ይህ አኗኗራችን አንዲት ዳቦን ለመግዛት ብቻ በሁለት ቶን የብረት ሳጥን (መኪና) ውስጥ ከመኖርያ ቦታችን ተነስተን ሦስት ኪሎሜትር  እንድንጓዝ አስገድዶናል።

​ይህ የኪን-ህንፃ እነ ስነከተማ ውድቀት ብቻ አይደለም፤ ጥልቅ ማህበራዊ እና አካባቢያዊ ውድቀትም ጭምር እንጂ።

መልካሙ ዜና ግን ምን ማድረግ እንዳለብን የምናውቅ ሲሆን ፣ ሁሉም የስነከተማ ማስተካከያ መሳሪያዎችም በእጃችን ይገኛሉ፡-

​✅ ከተበታተነ ወደ ተጠጋጋ (Compactness)
መስፋፋት የተገለሉ የቤት "ደሴቶችን" ይሰጠናል። መቀራረብ ግን ቢያንስ በካሬ ኪሎ ሜትር 15,000 ሰዎች የሚኖሩበት የተቀናጀ የከተማ ቅርጽ ይሰጠናል። ይህም የአካባቢ ሱቆች እና የሕዝብ ትራንስፖርት ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል።

​✅ ከረጅም ጉዞ ወደ እግር ጉዞ
በአሮጌው ሞዴል የረጅም መንገድ ተጓዦች እስረኞች ነን። በአዲሱ ሞዴል ግን የዕለት ተዕለት ፍላጎቶችዎ ከ5 እስከ 15 ደቂቃ የእግር ጉዞ ውስጥ ይሟላሉ—ይህም "የቤት-ሥራ-አገልግሎት" ሶስት ማዕዘንን (Home-Work-Service triangle)ያነቃቃል።

​✅ ከአንድ አገልግሎት ወደ ተቀናጀ ሕይወት (Mixed-Vibrancy)
አኗኗራችንን  በ ተለያዩ "ቀጠናዎች" መካከል መከፋፈል ማቆም አለብን። የመኖሪያ፣ የንግድ እና የሕዝብ ቦታዎችን በመቀላቀል፣ በቀን 24 ሰዓት ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ንቁ የሆኑ ጎዳናዎችን እንፈጥራለን።

​✅ በመኪና ከመመካት ወደ ምሉዕ ጎዳናዎች
የመስፋፋት ዘይቤ ለተሽከርካሪ  አውራ ጎዳናዎች ቅድሚያን ይሰጣል፤ የመቀራረብ ዘይቤ ግን ለሰው ልጅ ቅድሚያ በመስጠት ለእግር ጉዞ፣ ለብስክሌት እና ለቅርብ ግንኙነቶች አስተማማኝ መንገዶችን ያዘጋጃል።

​✅ ከጥቃት ተጋላጭነት ወደ ጽናት (Resilience)
የከተማ መስፋፋት ተፈጥሮን ይውጣል። መቀራረብ ግን ተፈጥሮን ከሰፈር ጋር ያዋህዳል፤ ይህም በመስፋፋት ምክንያት የሚመጣውን ሙቀትና የጎርፍ አደጋ ለመቀነስ ይረዳል።
​
Via UN-HABITAT

@etconp

Comments

Be the first to add a comment