👉በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ የፕሮጀክት መዘግየት የተለመደ ፈተና ቢሆንም፣ ከውል አንፃር ግን የራሱ የሆነ ከባድ የህግ እና የገንዘብ ተጠያቂነት አለው።
🌟አንድ ተቋራጭ (Contractor) ፕሮጀክቱን በውሉ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ( Completion Time) አጠናቆ ለEmployer/Client ሳያስረክብ ሲቀር፣ ለሚፈጠረው አላስፈላጊ መዘግየት የሚከፍለው የካሳ ቅጣት Liquidated Damages (ወይም በ FIDIC አጠራር Delay Damages) በመባል ይታወቃል።
ይህንን የካሳ ቅጣት በተመለከተ FIDIC Red Book 2017 አሰራር ግልፅ የሆኑ ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል።
🚥በውሉ Sub-Clause 8.2 መሠረት ተቋራጩ ሙሉውን ስራ ወይም በውሉ የተከፋፈሉ የፕሮጀክቱን ክፍሎች (Sections) በ Contract Data በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ አጠናቆ የማስረከብ ጥብቅ ግዴታ አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ጊዜው ካለፈ፣ በVSub-Clause 8.8 መሠረት ቀጣሪው በዘገየበት ቀናት ልክ የካሳ ቅጣቱን የማስፈጸም መብት ይኖረዋል።
⏺እርግጥ ነው፣ የቅጣቱ አጠቃላይ ድምር በ Contract Data ላይ ከተቀመጠው ከፍተኛ ገደብ (Maximum Amount) መብለጥ አይችልም፤ እንዲሁም ቅጣቱን መክፈሉ ተቋራጩ ስራውን አጠናቆ የማስረከብ ቀሪ የውል ግዴታዎቹን አያነሳለትም።
▶️ወደ PPA ስንመጣም ደግሞ፣ በመንግስት ፕሮጀክቶች ላይ ተግባራዊ የሚሆነው ይህ የ PPA Standard Bidding Document ይህንን ሃሳብ በግልፅ ይደግፈዋል።
☄በ PPA GCC መሠረት የ Liquidated Damages መጠን የሚሰላው በየቀኑ ከጠቅላላ የውል ዋጋው (Contract Price) በተወሰነ ፐርሰንት (በአብዛኛው 0.1%) ታስቦ ነው።
⏺በተመሳሳይ ሁኔታ የቅጣቱ ጣሪያ ከጠቅላላ የውል ዋጋው 10% መብለጥ የማይችል ሲሆን፣ የተቀጣው የካሳ መጠን ይህንን ከፍተኛ ገደብ ከነካ፣ ቀጣሪው ውሉን በተቋራጩ ጥፋት (Termination for Contractor's Default) ሙሉ በሙሉ ለማቋረጥ ህጋዊ መብት ያገኛል።
⏺በነዚህ የውል ማስፈፀም ሂደቶች ውስጥ የኮንትራት እና ሳይት ኢንጂነሮች ሚና ከፍተኛ ነው።
⏺ፕሮጀክቱን የሚቆጣጠሩ አማካሪ መሐንዲሶች (Consultants/Resident Engineers) የቅጣት መጠኑን በየወሩ ከሚዘጋጀው የክፍያ ሰርተፍኬት (Interim Payment Certificate - IPC) ላይ በመቁረጥ (Deduction) ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ።
⏺በሌላ በኩል ደግሞ ተቋራጩ ለዘገየበት ምክንያት የEmployer/client እጅ ካለበት ፣ ቅጣት ውስጥ ከመግባቱ በፊት ወዲያውኑ አግባብነት ያለው የጊዜ ማራዘሚያ (Extension of Time - EOT) ጥያቄ በማቅረብ መብቱን ማስጠበቅ ይኖርበታል።
━━━━━━━━━━━━━━━
👉የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሕግ እና አተገባበሩ | የተግባር መመሪያ መፅሐፍ ይፈልጋሉ?
📚 ይህ መፅሐፍ በኮንስትራክሽን ሥራ ውስጥ የሚመለከቱ የሕግ ጉዳዮችን በቀላልና ተግባራዊ መልኩ ለመረዳት ይረዳል።
⏺የኮንስትራክሽን ሕግ መሠረታዊ ግንዛቤ
⏺የግንባታ ፕሮጀክት ሕጋዊ አተገባበር
⏺የተዋዋይ ወገኖች መብትና ግዴታ
⏺የኮንትራት እና የስምምነት ጉዳዮች
⏺የግንባታ ሥራ ኃላፊነትና ተጠያቂነት
⏺በግንባታ ሥራ ላይ የሚፈጠሩ የሕግ ጉዳዮች እና ሌሎች ተካተዋል
👇
https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a83e1c10064f_etconp