የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
👉
የስጦታ ዉል ማለት ሰጪዉ ለሌላ ሰዉ ችሮታ በማድረግ ሃሳብ ከንብረቶቹ አንዱን የሚለቅበት ወይም ግዴታ የሚገባበት ዉል ስለመሆኑና ስጦታ ማድረግ የሰጪዉ የግል ተግባር ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2427 እና 2434 ይደነግጋል፡:
👉
ከዚህ እንደምንገነዘበዉ ስጦታ ዉል የጸና ዉል እንዲሆን እንደማናቸዉም የዉል ጉዳዮች በዉል ህግ የተደነገገዉን መሰረታዊ መስፈርት
አሟልቶ መገኘት ያለበት መሆኑን ነዉ፡:
👉
የስጦታ ዉሉ በህግ የተመለከተዉን መሰረታዊ መስፈርት እና ስለስጦታ ዉል የተደነገጉትን ደንቦች አላሟላም በሚል መብትና ጥቅሙ የተነካበት ወገን ዉሉ እንዲፈርስ ሊጠይቅ እንደሚችል ከዉል ህጎች ጠቅላላ ድንጋጌ እና ስለስጦታ ዉሎች ከተደነገገዉ ልዩ ከፍል መገንዘብ ይቻላል።
👉
በመሰረቱ አንድ ዉል እንዲፈርስየሚደረገዉ ዉሉ የተቋቋመበት ሁኔታ ከመሰረቱ ግድፈት ሲኖርበት ነዉ።
👉
ይኸዉም የተዋዋይ ወገን ለመዋዋል ችሎታ ወይም ፈቃድ ጉድለት ሲኖር ወይም የዉለታዉ ጉዳይ ህግን ወይም ግብረ ገብነት/ሞራል/ የሚጻረር ሲሆን ወይም በህግ የተደነገገዉን ፎርም ሳያሟላ ሲቀር ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1808 ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡
👉
ከእነዚህ ምክንያቶች በአንዱ ወይም በሌላ ሁኔታ ዉሉ ጉድለት አለበት በሚል ዉሉ እንዲፈርስ መጠየቅ የሚችለዉ ወገን ማንነት እንደየምክንያቱ የሚለያይ መሆኑም በዚሁ ድንጋጌ ላይ ተመልክቷል።
👉
ይህ እንደ አጠቃላይ ሆኖ የስጦታዉ ዉል ሊፈርስ የሚችልባቸዉ ልዩ ሁኔታዎች በህጉ አንቀጽ 2437 እስከ 2440 ላይ ተዘርዝረዋል፡፡
👉
በዚህም መሠረት የስጦታ ዉል ሊፈርስ የሚችለዉ ስጦታዉ በተደረገበት ወቅት ስጦታ አድራጊዉ የአእምሮ ችግር እንዳለበት ታዉቆ በፍርድ ክልከላ የተደረገበት (judicial interdiction) ወይም ስጦታዉ የተደረገዉ ስጦታ ሰጪዉ የፍርድ ክልከላ እንዲደረግበት ለፍርድ ቤት ጥያቄ ከቀረበ በኋላ ወይም ስጦታዉ ሲደረግ የስጦታ ሰጪዉ አእምሮ ጤነኛ አለመሆኑን የዉሉ ይዘት የሚያሳይ ሲሆን፣ ስጦታዉን ለማድረግ መነሻ
የሆነዉ ምክንያት ከህግ ወይም ከሞራል ተቃራኒ ከሆነ፣ ስጦታዉ ሲደረግ ስጦታ ሰጪዉ
በመንፈስ ጫና (undue influence) ስር መሆኑ ከተረጋገጠ ስለመሆኑ ከድንጋጌዎች ይዘትመገንዘብ ይቻላል፡፡
👉
ስለሆነም የስጦታ ዉል እንዲፈርስ ለፍርድ ቤት ጥያቄ የሚያቀርብ ሰዉ ከእነዚህ ሁኔታዎች ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሁኔታ መኖሩን የመግለጽ እና ይህንኑ የማረጋገጥ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
👉
የሰ/መ/ቁ.200144 ቀን፡- 02/02/2014ዓ.ም
Comments
Be the first to add a comment