ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4848 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ (399) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4469 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 195 ወንድ እና 204 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ4 እስከ 85 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 398 ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 የውጭ ዜጋ ነው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 135 ሰዎች ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ፣ 132 ሰዎች ከደዋሌና ጋሊሌ ለይቶ ማቆያ፣ 86 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 18 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 14 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ 9 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 1 ሰው ከደቡብ ክልል፣ 1 ሰው ከጋምቤላ እና 1 ሰው ከሱማሌ ክልል ናቸው።

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ዘጠና አምስት (95) ሰዎች (82 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከአማራ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል ፣ 1 ከትግራይ ክልል፣ 1 ከኦሮሚያ ክልል እና 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1122 ነው።

@TenaET

2 comments

محمد راضي
የሞተ የለም