የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሌላው ልብ ልንለው የሚገባው አጥፊው ጉዳይን ያለአግባብ ማጓተት ፈጽሟል ለማለት የተላለፈው ግልጽ የሆነ በህግ፣ በመመሪያ እና በአሰራር ደንብ የተቀመጠ ምክንያታዊ የውሳኔ መስጫ ጊዜን በመተላለፍ ውሳኔውን በሰአቱ ሳይሰጥ የቀረ መሆኑን በማስረዳት ነው፡፡ በዚህም እንደየሙያና አገልግሎት መስኩ ውሳኔ ሊሰጥበት የሚገባው ጉዳይ የሚፈልገውን ምክንያታዊ ጊዜ ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡

ማጠቃለያ
የመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆኑ የህዝባዊ ድርጅቶች ተገልጋዮቻቸውን ሲያስተናግዱ አገልግሎት ወይም ውሳኔ የሚሰጥበት ጉዳይ ያለውን ልዩ ባህሪ ግምት ውስጥ በማስገባት በህግ እና በአሰራር ስርአት እንዲሁም የተለመዱ አካባቢያዊ ሀኔታዎችን በማገናዘብ ለተገልጋዮቻቸው በተገቢው ጊዜ ውሳኔ የመስጠት ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ያለ በቂ ምክንት ህግ እና አሰራርን በመጣስ ተገልጋዮችን ለማንገላታት እና ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት እንዲሁም አግልግሎት ጠያቂው ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ጉዳይን ያለበቂ ምክንያት ማጓተት በህግ የሚያስጠይቅ እና የሚያስቀጣ የወንጀል ተግባር መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ ተገልጋዩ ማህበሰረብ በመንገስትም ይሁን ህዝባዊ ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት ሲሄድ በህግ እና አሰራር ስርአት የተቀመጡ የአሰራር ደረጃዎችን ተረድቶ በዛ ውስጥ ውሳኔ እንዲያገኝ መጠየቅ እና ይህ በማይሆንበት ጊዜ ጉዳዩን ያለ በቂ ምክንያት የሚያጓትቱ የመንግስት እና ህዝባዊ ድርጅት ሰራተኞች እና ሀላፊዎች ላይ የህግ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ከፍትህ አካላት ጋር በመተባበር መስራት ያስፈልጋል፡፡

Comments

Be the first to add a comment