👉ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለሚገኘው የቤት ልማት ፕሮግራም በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩ ስራ ተቋራጮችን ይጋብዛል።

1. የሚያስፈልጉ ሰነዶች፡
ሀ) የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እና የአቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገብ ማረጋገጫ።
ለ) የሰነዶቹን ዋና እና አንድ ቅጂ በአካል የሚቀርቡ ሆነው፣ በባለቤት ወይም በህጋዊ ውክልና ተወካይ ፊርማ እና በድርጅት ማህተም የተፈረሙ።

2. ተሳታፊነት፡ ከደረጃ 1-4 ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GC)፣ ህንፃ ተቋራጭ (BC) እና ደረጃ 5 የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው ስራ ተቋራጮች።

3. የምዝገባ ጊዜ እና ቦታ፡ ከቅዳሜ 9/12/2018 ዓ.ም (ከጠዋቱ 2:30) እስከ ሀሙስ 14/12/2018 ዓ.ም (ከሰዓት 11:30) በ5 ቀናት፣ በኮርፖሬሽኑ 11ኛ ወለል አዳራሽ። የቴክኒካል ሰነድ መግዛት ይቻላል።

4. ውጤት፡ ምዝገባ በተጠናቀቀ በ24 ሰዓት ውስጥ በቀን 15/12/2018 ዓ.ም በማህበራዊ ድረ-ገጽ እና በ11ኛ ወለል የማስታወቂያ ቦርድ ይለጠፋል።

5. የቴክኒካል ፕሮፖዛል ማስገባት፡ ከውጤቱ ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ፣ እስከ 27/12/2018 ዓ.ም ከሰዓት 11:30 ድረስ፣ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ቅጂ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት።

6. ክፍያ፡
- ደረጃ 1፡ 7,500 ብር
- ደረጃ 2፡ 6,500 ብር
- ደረጃ 3፡ 5,500 ብር
- ደረጃ 4፡ 5,000 ብር
- ደረጃ 5፡ 4,500 ብር

አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ተማ፣ ወረዳ 01፣ ባምቢስ አከባቢ፣ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ህንፃ፣ 11ኛ ወለል።

ነሀሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን፣ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

@etconp

Comments

Be the first to add a comment