የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ጤና ይስጥልኝ!!!
ባንያዝ የተያዘ፣ ባንከሰስ የተከሰሰ ሰው እናውቃለን፤ እታዲያ በኢፌድሪ ሕገመንግስትና በወንጀል ሕጉ ስለነዚሁ ሰዎች እውቅና የተሰጣቸው መብቶች በጥቂቱ በአንቀጽ 18 / 19 እንዲህ በአጭሩ እንይ!፡
ሲያዙ ሰብዓዊ ክብራቸው እንዲጠበቅ፤
ለምን እንደተያዙ በሚገባቸው ቋንቋ እንዲነገራቸው፤
ካልፈለጉ ያለመናገር መብት እንዳላቸው፣ የሰጡት ቃል ለፍርድ ቤት በነሱ ላይ ማስረጃ ሆኖ እንደሚቀርብ ሊነገራቸው እንደሚገባ፤
ጠበቃቸውን ሳያገኙ ቃል ያለመስጠት መብት እንዳላቸው፤
ተገደው ስለማንም ምስክርነት ያለመስጠት መብት እንዳላቸውከመደንገጉም በተጨማሪ፤
በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ፣ በነሱ ላይ የተመሰረተውን ክስ የማየት፣ ምስክሮችን የመጠየቅ
የመከላከያምስክሮችን የማቅረብ፣ክሳቸው በግልጽ ችሎት የመታየት መብት አላቸው፡፡
ከተፈረደባቸውም ሆነ በክስ ላይ እያሉ ከጉልበት ብዝበዛ፣ ከኢሰብዓዊ አያያዝ የመጠበቅ፣ ክብርን ከሚያዋርድ ተግባርና አያያዝ ነጻ የመሆን፣ በፍርድ ቤት ከታዘዘባቸው ተግባር ውጭ ስራ ያለመስራት መብት አላቸው፡፡
ለፍትሕ የራሳችንን ድርሻ እንወጣ!!!
ቸር ይግጠመን!
ሲሳይ ሰማኝ
የካቲት 15/06/2014 ዓ.ም
Comments
Be the first to add a comment