⭐️የህዳስያችን ኮርቻ ግድብ (Saddel Dam)

💫ከወንዙ ፍሰት አቅጣጫ አንፃር በስተግራ በኩል የሚገኝ የግድቡ ክፍል ነው።

⏺5.2 ኪሎሜትር ርዝመት እና 50 ሜትር ከፍታ አለው።

⏺ግንባታው የተካሄደውም በአለት ሙሊት /Rock fill ሲሆን ውሃው በሚተኛበት ገፁ በኩል ያለው ክፍሉ በ30 ሳንቲ ሜትር ውፍረት ባለው ኮንክሪት ተለብጧል።

🎲ግድቡን ለመስራት 15 ሚሊዮን ሜትር ኪዮብ የዐለት ስብርባሪ ጥቅም ላይ ውሏል።

▶️የኮርቻ ግድብ ዋና ጥቅም ከዋናው ግድብ ከ90 ሜትር በላይ ማለትም ከ590 masl አልፎ የሚሞላው ውሃ ከግድቡ ሾልኮ እንዳያመልጥ ለመያዝ ነው።

⏺የኮርቻ ግድቡ አጠቃላይ የ grouting / ስርገት መከላከል ስራም ተሰርቶለታል። ጤንነቱን የሚቆጣጠር inspection gallery አለው። በ inspection gallery ውስጥም የግፊት / pressure ፣ የውሃ መጠን / water level ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ / earthquake ፣ ...መለካት የሚችሉ መሣሪያዎች ተገጥመውለት የግድቡን ጤንነት ይቆጣጠሩበታል። 

⚫️ የኮርቻ ግድብ ምን ፋይዳ አለው?

የኮርቻ ግድብ ኃይል ለማመንጨት የተጠራቀመውን ውሃ አቅፎ የሚይዝ ነው።

ብዙም ያልተነገረለት የኮርቻ ግድብ ባይገነባ ኑሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አቅም ከታች ያስቀመጥኩት ነጥቦች ላይ ይመሥል ነበር።

👉 የዋና ግድብ ከፍታ 90 ሜትር / 590masl ላይ ይወሰን ነበር።

👉 ግድቡ የማምነጨት አቅሙ 1400MW ብቻ ይሆን ነበር።

👉 ዋናው ግድብ የሚይዘው ውሃ 16 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ላይ ብቻ ይወሰን ነበር።

⚫️ የኮርቻ ግድቡ በመገንባቱ ምክንያት :-

👉 የግድቡን ከፍታ ወደ 145 ሜትር / 645 masl ጨመረ።

👉 ኃይል የማመንጨት አቅሙን ወደ 5150 ሜጋ ዋት አደገ።

👉 ግድቡ የሚይዘውን ውሃ መጠን በአምስት አጥፍ ጨምሮ 74 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ከፍ አለ።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment