ኢትዮጵያ ትገነባለች! 🏗️🇪🇹

የሀገራችንን የኮንስትራክሽንና የመሠረተ ልማት ገጽታ የሚቀይር ታላቅ ሳምንት ተደግሷል።

የኢትዮጵያ የመሠረተ ልማትና የኮንስትራክሽን ሳምንት "ኢትዮጵያ ትገነባለች!" በሚል መሪ ቃል ከነገ ማለትም ከሚያዚያ 9/ 2018 ጀምሮ እስከ ሚያዝያ  12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል  ደማቅ ዝግጅት እንደሚካሄድ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ይህ ታላቅ መድረክ :-

🔹 የቴክኖሎጂ ማዕከል፦ ከግንባታ እቃዎች እስከ ግዙፍ ማሺነሪዎች፣ ዘመናዊ ዲጂታል የግንባታ ቴክኖሎጂዎችና ዘላቂ መፍትሔዎች ለዕይታ ይቀርባሉ።

🔹 የገበያ ትስስር፦ የሀገር ውስጥ አምራቾች ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበትና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በፍጥነት በማደግ ላይ ወዳለው የኢትዮጵያ ገበያ የሚገቡበት ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል።

🔹 ዕውቀትና ፈጠራ፦ የዘርፉ ተዋናዮችና የፈጠራ ባለቤቶች ልምድ የሚለዋወጡበትና አዳዲስ አሰራሮችን የሚቀስሙበት መድረክ ነው።

🔹 ሥራ ዕድል፦ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚታይበትና ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥረው ይህ ዘርፍ ያለበት ደረጃ በዝርዝር ይቃኛል።

ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በመግለጫቸው እንደጠቀሱት፤ ዝግጅቱ የግንባታ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካትና ፍትሐዊ የመሠረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጉዞ የሚያፋጥን ነው። ስለሆነም መላው የማህበራችን አባላቶች
የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ባለሀብቶችና ግንባታ ወዳዶች በሙሉ ቀጠሯችሁ በዚሁ ኤግዚብሽን እንዲሆን እንጋብዛለን!

@etconp

Comments

Be the first to add a comment