👉የሕንፃ ግንባታ ደህንነትን ሳይጠብቁ በሚሠሩ አልሚዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ ተወሰደ!

​በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሕንፃ ግንባታ ደህንነት መስፈርቶችን ሳያሟሉ፣ ለአደጋ አጋላጭ በሆነ መልኩ ግንባታ ሲያካሂዱ በተገኙ አልሚዎች፣ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ላይ የገንዘብ ቅጣትና አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ። ⚠️

​በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ዘርፍ ዋና ዳይሬክተር ም/ል ኢ/ር አመለወርቅ አሰፋ እንዳስታወቁት፤ በተደረገው ድንገተኛና ሰፊ የክትትል ሥራ ሕግን በጣሱ አካላት ላይ የሚከተሉት እርምጃዎች ተወስደዋል፦

​💰 የገንዘብ ቅጣት፦ የሕንፃ ደህንነት መስፈርቶችን ባላሟሉ አልሚዎች ላይ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት የገንዘብ ቅጣት ተጥሏል።

​⚙️ አስተዳደራዊ እርምጃ፦ ኃላፊነታቸውን ባልተወጡ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ላይ ተመጣጣኝ አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃዎች ተወስደዋል።

​🚨 የባለሥልጣኑ ማሳሰቢያ፦ "የሕንፃ ደህንነት መስፈርቶችን በመጣስ የሚፈጸሙ ግንባታዎች በሠራተኞችና በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ሕይወት የመጥፋት፣ የአካል መጉደል እንዲሁም በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

የሕንፃ ግንባታ ደህንነትን ማስጠበቅ የሁሉም ኃላፊነት ነው፤ ሕግን ማክበር ሕይወትን ይጠብቃል!"
​የቁጥጥር ሥራው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን፤ ሁሉም አልሚዎች፣ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ጥንቃቄ አድርገው ሕንፃ ግንባታ ደህንነትን ሙሉ በሙሉ አሟልተው እንዲሠሩ ጥሪ ቀርቧል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment