👉ለጠቅላላ እውቀት
💫ስለ CGPA እና GPA አሰራር ማብራሪያ
🚧ብዙዎች እንደሚሳሳቱት፣ Cumulative GPA (CGPA) ማለት የ-1st Semester እና የ-2nd Semester Gpaን ደምሮ ለሁለት ማካፈል ማለት አይደለም
❌🏷የትኛውም የGPA ስሌት የሚሰራው ተማሪው በወሰዳቸው አጠቃላይ Credit Hours ብዛት ላይ ተመስርቶ ነው።
📚 የሴሚስተር GPA አሰራር
🧷የአንድን ተማሪ የሴሚስተር ውጤት (GPA) ለማስላት፣ እያንዳንዱ ትምህርት ያለው የ Credit Hour በዛው ትምህርት የመጣው Grade Point ይባዛል። ከዚያም የሁሉም ትምህርቶች ውጤት በአንድ ላይ ተደምሮ፣ በሴሚስተሩ ለተወሰዱት አጠቃላይ የ Credit Hour ድምር ይካፈላል።
🔖ምሳሌ፦ አንድ ተማሪ በሴሚስተሩ 3 ትምህርቶችን ቢወስድ፡
1ኛ ትምህርት፦ Grade A (4.0) እና Credit Hour 5 ቢሆን ➔ 4.0 x 5 = 20
2ኛ ትምህርት፦ Grade A- (3.75) እና Credit Hour 5 ቢሆን ➔ 3.75 x 5 = 18.75
3ኛ ትምህርት፦ Grade B (3.0) እና Credit Hour 3 ቢሆን ➔ 3.0 x 3 = 9
🚧የተማሪውን GPA ለማግኘት፦
የውጤቶች አጠቃላይ ድምር፦ 20 + 18.75 + 9 = 47.75
የአጠቃላይ Credit Hour ድምር፦ 5 + 5 + 3 = 13
🔗በመጨረሻም፣ የውጤቱን ድምር ለአጠቃላይ ክሬዲት ሰዓቱ ስናካፍለው የሴሚስተሩን GPA እናገኛለን፦
47.75 ÷ 13 = 3.67
❇️ስለዚህ፣ ይህ ተማሪ በሴሚስተሩ 3.67 GPA አመጣ ይባላል።
🪧CGPA ሲሰላም በተመሳሳይ መንገድ የሁሉንም ሴሚስተሮች(የሁሉንም ኮርሶች) አጠቃላይ የውጤት ድምር ለአጠቃላይ የክሬዲት ሰዓት ድምር በማካፈል ነው የሚገኘው።
📌 የ CGPA አሰራር ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ፦
🚧ለምሳሌ የአንድን ተማሪ የሁለት ሴሚስተር የCGPA ውጤት ለማስላት፦
• 1st Semester ላይ፦
የውጤት ድምር = 47.75
የ Credit Hour ድምር = 13
(GPA = 3.67)
• 2nd Semester ላይ፦
የውጤት ድምር = 52.00
የCredit Hour ድምር = 15
(GPA = 3.46)
❌ የተሳሳተው አሰራር፦ የሁለቱን ሴሚስተር GPA ደምሮ ለሁለት ማካፈል (3.67 + 3.46) ÷ 2 = 3.56 (ይህ ስህተት ነው!) የምትወስዱት ኮርስ በጨመረ ቁጥር የተሳሳተ Result ነው የምታገኙት
🔗ትክክለኛው አሰራር (CGPA)፦
የሁለቱንም ሴሚስተር አጠቃላይ የውጤት ድምር ለአጠቃላይ የክሬዲት ሰዓት ድምር ማካፈል፦
• አጠቃላይ የውጤት ድምር፦ 47.75 + 52.00 = 99.75
• አጠቃላይ የCredit Hour ድምር፦ 13 + 15 = 28
🔗ስለዚህ CGPA = 99.75 ÷ 28 = 3.562 (ወደ ሁለት Digit ሲጠጋ 3.56 ይሆናል።)
📎ውጤቱ ተመሳሳይ ሊሆን የቻለው የሁለቱ ሴሚስተሮች የክሬዲት hr በጣም ስለሚቀራረብ ብቻ ነው፤ የምትወስዷቸው ኮርሶች በበዙ ቁጥር የ ሁለቱ አሰራር ልዩነት ይፈጥራል።
@etconp