👉የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ ሒሳብ ሲቀርብ መሟላት ያለባቸዉ ሰነዶች

1. ዓመታዊ ሽያጭ ማጠቃለያ (summery report)
2. ከሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ዉጪ የእጅ በእጅ ደረሰኝ የተደረገ ሽያጭ ካለ ማጠቃለያ ሪፖርት
3. ድርጅቱ ከሚጠቀምበት ባንክ የባንክ ስቴትሜንት
4. የሂሳብ መግለጫዎች ማለትም የትርፍና ኪሣራ መግለጫ (Profit and loss statement) ፣የሀብት እና የዕዳ መግለጫ (balance sheet) ፣ የጥሬ ገንዘብ ገቢ እና ወጪ መግለጫ (Cash flow statement)፣የባለቤቶቹ ሁኔታ (owners’ equity position) እንዲሁም የመረጃ ቋት(Ledger)
5. ተከፋይ ሂሳብ(withholding tax) ካለ ማጠቃለያ ሪፖርት እና ዋናዉን ደረሰኝ
6. ለጥገናና ማሻሻያ የወጡ ወጪዎች ለየትኛዉ ቋሚ ዕቃ መጠገኛ ስለመዋሉ የሚያስረዳ ማስረጃና ማጠቃለያ ሪፖርት
7. የቋሚ ንብረት ደረሰኝ ወይም ማስረጃ
8. የእርጅና ቅናሽ የተያዘለት የንግድ ሥራ ሀብት በሠንጠረዥ የተሰላ ቅጽ
9. የተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦች ዝርዝር መግለጫ
10. በግብር እፎይታ ላይ ያለ ግብር ከፋይ ይሄንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ
11. ለበጎ አድራጎት ዓላማ የሚደረጉ ስጦታዎች ካሉ ለበጎ አድራጎት የተቋቋመ ድርጅት መሆኑን የሚያሳይ መረጃ እንዲሁም የጥሪ ደብዳቤና ገቢ የተደረገበት የባንክ ስሊፒ
12. የየወሩን VAT ሪፖርት ዝርዝር መረጃ የሚያሳይ ኤክሴል
13. ኦንላይን ያሳወቁበት ዓመታዊ ሪፖርት ሀርድ ኮፒ
14. በኦዲት ቦርድ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ቅጂ
15. ሒሳቡ በተፈቀደላቸዉ የሒሳብ አዋቂዎች የተሠራ ከሆነ የሒሳብ ሠራተኛዉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቅጂ
16. ሂሳቡ በድርጅቱ የሒሳብ ሠራተኛ የተሠራ ከሆነ የሂሳብ ሠራተኛዉ የትምህርት ማስረጃ እና ተቀጣሪ መሆኑን የሚያመላክት መረጃ ተያይዞ መቅረብ አለበት
17. ዓመታዊ ሂሳብ ማሳወቂያ ቅጽ ከደንበኞች አገልግሎት ወስዶ መሙላት ያስፈልጋል፡፡

▫️ በሠንጠረዥ ‘ሐ’ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታ ያለበት እና ከአንድ በላይ የንግድ ሥራ መስክ ገቢ የሚያገኝ የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋይ፣ በዚህ አዋጅ እና በሌሎች ተፈጻሚነት ባላቸው ሕጎች መሠረት ለእያንዳንዱ የተለየ የሥራ መስክ የሂሳብ መዝገቦችን እና ደጋፊ መረጃዎችን በተናጠል መያዝ አለበት።(በ1395/2017 መሠረት)

@etconp

Comments

Be the first to add a comment