👉የቤተሰብ ቁጥር ዕድገት በመጨመሩ ዓመታዊ የቤት ፍላጎት 486,000 መድረሱ ተነገረ

🚧በየዓመቱ አዳዲስ የሚመሠረት የቤተሰብ ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ፣ ዓመታዊ የቤት ፍላጎት በሁለት እጥፍ አድጎ 486,000 መድረሱንና አቅርቦቱ ከፍላጎቱ አኳያ በግማሽ እንደሚያንስ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በኢትዮጵያ ያልሙ (Investin Ethiopia) በሚል መሪ ሐሳብ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ፎረም በማስመልከት የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የአውሮፓ ንግድ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የአገሪቱን የኢንቨስትመንት ዘርፍ አጠቃላይ መረጃዎችን ያካተተ ሰነድ በጋራ አዘጋጅተዋል፡፡

በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት ከሚተገበሩ የመንግሥት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የቤት ግንባታን በሚመለከት ባብራራው የሰነዱ ክፍል፣ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ የቤት ፍላጎት እየጨመረ መሆኑንና በዓመት 486,000 መድረሱ ተመላክቷል፡፡

በየዓመቱ የሚመሠረተው አዲስ የቤተሰብ ቁጥር እያደገ መምጣት፣ በየዓመቱ አምስት በመቶ የሚጨምረው ፈጣን የከተማና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ለቤት ፍላጎት መጨመር ዋና ዋና ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

መንግሥት በየዓመቱ ለሚያድገው የቤት ፍላጎት የሚያቀርበው 165,000 ቤቶችን መሆኑን፣ ይህም ከፍላጎቱ አኳያ ግማሽ ያህሉን እንኳን እንደማያዳርስ ሰነዱ ያመላክታል፡፡

የቤት ፍላጎቱ በየጊዜው ዕያደገ በመምጣቱ ከፍተኛ እጥረት መከሰቱን የሚጠቁመው ሰነዱ፣ ይህም ጠንካራና ቀጣይነት ያለው ፍላጎት ስለሚፈጥር፣ ኢንቨስተሮች በመንግሥትና በግል አጋርነት የቤት አቅርቦት ፕሮጀክቶች መሠረት ተመጣጣኝ፣ መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርግና ለኪራይ አገልግሎት የሚውሉ የቤት...

🔗 ተጨማሪ ያንብቡ👇 https://ethiopianreporter.com/153967/

@etconp

Comments

Be the first to add a comment