በኢትዮጵያ ተጨማሪ 195 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,853 የላብራቶሪ ምርመራ 195 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,954 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 90 ወንድ እና 105 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 95 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉ። ኢትዮጵያውያን ናቸው።


ቫይረሱ የተገኘባቸው 144 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 12 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 12 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 7 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ ፣ 7 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፣ 4 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 3 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል እና 2 ሰዎች ከሐረሪ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች (73 ከአዲስ አበባ፣ 5 ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአማራ ክልል እና 2 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 934 ደርሷል።
@tenaet
https://tena.et/update

Comments

Be the first to add a comment