የዳንጎቴ የ17 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት በኬንያ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው!
ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ በኬንያ ላሙ ካውንቲ ለመገንባት ያቀዱት ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት በአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾችና በነዋሪዎች ተቃውሞ እየገጠመው ይገኛል።
ስለ ፕሮጀክቱ ምን እናውቃለን?
አቅም: በቀን 700,000 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ የማጣራት አቅም ይኖረዋል ተብሎ ታቅዷል።
ኢንቨስትመንት: ከ15 እስከ 17 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት በምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ የሚባል ፕሮጀክት ነው።
ለምን ተቃውሞ ተነሳ?
የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች፣ በተለይም ግሪንፒስ አፍሪካ፣ ፕሮጀክቱ የሚከተሉትን ጉዳቶች ያስከትላል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል፦
⚠️ የአካባቢ ብክለት: በላሙ የሚገኙ የማንግሩቭ ደኖችን፣ የኮራል ሪፎችንና የባህር ውስጥ የዱር እንስሳትን ሊጎዳ ይችላል።
⚠️ የካርቦን ልቀት: ከፍተኛ የሆነ የበካይ ጋዝ ልቀትን ያስከትላል።
የአካባቢው ነዋሪዎች ስጋት
ቀደም ሲል በአካባቢው የተሰሩ ሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶች፦
ለነዋሪዎች የፈጠሩት የሥራ ዕድል አነስተኛ መሆኑ፣
የመሬት ይገባኛል ውዝግብ መፍጠራቸው፣
እንዲሁም የአካባቢ ብክለት ማስከተላቸው በአሁኑ ፕሮጀክት ላይ ትልቅ ጥርጣሬ ፈጥሯል።
በመሆኑም፣ መንግስት ገለልተኛ የሆነ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ (Environmental Impact Assessment) ሳይከናወን ለፕሮጀክቱ ፈቃድ እንዳይሰጥ ተሟጋቾች ጥሪያቸውን እያቀረቡ ነው።
@etconp