ክስ የማቅረብ መብት (Locus standi/the law of standing) የህዝብ ጥቅምን (public interest) በሚመለከቱ ጉዳዮች
#በዳንኤል ፍቃዱ የህግ ቢሮ
> በከሳሽ ተሰይሞ ክስ በችሎት (ፍርድ ቤት) የማቅረብ መብትን የሚመለከት ነዉ፡፡ አንድ ሰዉ ክስ የማቅረብ መብት አለዉ ለማለት የሚቻለዉ፡-
> ለክሱ ምክንያት የሆነዉ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተዉ መሆኑ፤
> ክሱ ለክሱ መነሻ የሆነዉ ጉዳት መከሰቱን የሚያሳይ፤
> በህግ ዕዉቅና የተሰጠዉ (ሊፈጸም የሚችል) መብት መኖሩ፤
> የባህላዊ ክስ የማቅረብ መብት (Traditional Locus Standi) በተለምዶ፣ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት (locus standi) የሚኖረው በቀረበው ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ የግል ጥቅም ወይም ጉዳት (direct personal interest) ላለው አካል ብቻ ነው። ይህ አቀራረብና ዓላማው ግብረገብ ወይም የሕግ አጠቃቀምን የሚጠይቁ ጉዳዮች በተመለከተ ብቻ ነው።
• ይሁንና ክሱ የህዝብ ጥቅምን (public interest) የሚመለከት ሲሆን ለክሱ ምክንያት የሆነዉ በቀጥታ ከሳሽን የሚመለከተዉ ባይሆንም ክስ ማቅረብ እንደሚቻል በጊዜ ሂደት ተቀባይነት እያገኘ የመጣ አሠራር ነዉ፡፡
• በርካታ አገራት በህገ መንግስቶቻቸዉ ይህን አመላክተዋል፡፡
• ክስ የማቅረብ መብት ከአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 11(3) አንፃር፡-
> 11(4)- ማንኛዉም በጉዳዩ መብት ወይም ጥቅም ያለዉ ሰዉ ወይም ጉዳዩን ለማቅረብ በቂ ምክንያት ያለዉ ሰዉ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶችን ለማስከበር አቤቱታ የማቅረብ መብት አለዉ፡፡
> ከዚህ መገንዘብ የሚቻለዉ አንድ ሰዉ ለክሱ ምክንያት በሆነዉ ጉዳይ ላይ መብትና ጥቅም ያለዉ መሆኑን ማሳየት ሳይጠበቅበት ክሱን ለማቅረብ በቂ ምክንያት ያለዉ መሆኑን ካሳየ ክስ ማቅረብ የሚችል መሆኑን ነዉ፡፡
> ማንኛዉም ሰዉ በፍርድ ሊወሰን የሚገባን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በህግ የመዳኛት ስልጣን ላለዉ አካል የማቅረብ ዉሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለዉ፡፡አንቀጽ 37 የዜጎች ፍትህ የማግኘት መብትን ተመላክቷል፡፡
> የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 11 (3) ነዉ፡፡ “…በዚህ አዋጅ ሌሎች ድንጋጌዎች እንዲሁም በሌሎች ህጎች የተመለከተዉ ቢኖርም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍርድ ታይተዉ ሊወሰኑ የሚችሉ በሕገ መንግስቱ ምዕራፍ ሦስት (ከአንቀጽ 13 እስከ 44- ስር የተመለከቱ መሰረታዊ መብቶች እና ነጻነቶችን ለማስከበር ለጉዳዩ ተገቢ የሆነ ፍርድ፣ ትዕዛዝ ወይም ዉሳኔ ለመስጠት ስልጣን አለዉ፡፡ (Notwithstanding the provisions of this proclamation and other relevant laws, the Federal High Court can render decisions, judgments or order in order to protect justiciable human rights specified under chapter three of the Constitution).
> በፍርድ ታይተዉ ሊወሰኑ የሚችሉ መብቶች የትኞቹ ናቸዉ? ሲቪል ወይም ፖለትካ መብቶች ነዉ ወይስ የትኖቹ ናቸዉ?በዚህ ላይ አዋጁ ላይ ምንም አልተባለም፡፡የሌሎች ሀገራትን ለምሳሌ በፍርድ ታይተዉ ሊወሰኑ የሚገቡት ጉዳዮች ተለይተዉ በህጋቸዉ ተደንግጎ ይገኛሉ፡፡
> በቂ ምክንያት ማለትስ ምንድን ነው? አከራካሪ ሃሳብ በመሆኑ ለፍርድ ቤት ትርጉም ክፍት ሆኗል፡፡

Comments

Be the first to add a comment