የእኩልነት መብት ከሰው ልጅ ተፈጥሮ ከሚመነጩ እና ከማይገረሰሱ አለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች አንዱ ነው። ሰዎች ሁሉ በህግ ፊት እኩል ናቸው የሚለው መርህ የመጣውም ከዚሁ የእኩልነት መብት ነው። በህገ መንግስቱ አንቀፅ 25 ስር እንደተደነገገው ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው፤ በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በህግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል። በመሆኑም በዘር፣ በብሄር፣ ብሄረሰብ፣ በቀለም፣ በፆታ፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ ዋስትና የማግኘት መብት እንዳላቸው ተደንግጓል። የወንጀል ህጉ አንቀጽ 4 ይህንን መርህ በተመሳሳይ ሁኔታ ያስቀመጠ ሲሆን
አድራጊዎች መሐከል ልዩነት የሚደረገው ምንጩ የአለም አቀፍ ህግ ወይም ህገ መንግስት ሆኖ በወንጀል ህጉ የተደነገገ መሰረታዊ መብት ሲኖር ወይም የወንጀሉ ከባድነት፣ የጥፋቱ ደረጃ ወይም የአድራጊው ዕድሜ፣ ሁኔታ ወይም ልዩ ግላዊ ጠባዩ ወይም ወንጀሉ በሕብረተሰብ ላይ ያስከተለው አደጋ ከግምት ውስጥ እንዲገባ ህጉ ሲደነግግ እንደሆነ ያስቀምጣል።

ከላይ ከተዘረዘሩት የወንጀል ህግ መርሆች በተጨማሪ ሁሉም ተጠርጣሪዎች እና ተከሳሾች ጥፋተኝነታቸው እስኪረጋገጥ ድረስ ንፁህ ሆነው የመገመት (Presumption of innocence)፣ ዝም የማለት መብት (the right to remain silent) እና ሌሎችም የተያዙ እና የተከሰሱ ሰዎች መብቶች በህገ መንግስቱ ተደንግገው ይገኛሉ።

ማጠቃለያ

በህገ መንግስቱም ሆነ በወንጀል ህጉ የተመለከቱ የወንጀል ህግ መርሆች ከላይ የተብራሩት ሲሆኑ ህግ አስከባሪ አካላት የወንጀል ምርመራ እና ክርክር ሥራዎችን ሲያከናውኑ እነዚህን የወንጀል ህጉን መርሆች በጥብቅ መከተል ይጠበቅባቸዋ::
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

Comments

Be the first to add a comment