​ቢሾፍቱ፤ የአፍሪካ የቱሪዝም ከተማ
​
​ቢሾፍቱ በ1917 ዓ.ም የተቆረቆረች ከተማ ስትሆን፣ ስሟን ያገኘችው ካሏት የተፈጥሮ ሀይቆችና የውሃ ሀብቶች የተነሳ “ቢሻኖፍቱ” (ውሃማ) ከሚለው ቃል ነው። ቢሾፍቱ የታሪክና የኦሮሞነት እሴቶች መገኛ፣ እንዲሁም ከሁሉም አቅጣጫዎች የሚመጡ ኦሮሞዎች በዓመት አንድ ጊዜ ተገናኝተው ፈጣሪን የሚያመሰግኑበት የኢሬቻ በዓል የሚከበርባት የምስጋና ምድር ናት።

​ቢሾፍቱ እንደሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ሁሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገት እያሳየች ያለች ከተማ ስትሆን፤ በተፈጥሮ ሀብቷ፣ በባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶቿ እንዲሁም ለአገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባና ለሸገር ከተማ ባላት ቅርበት የተነሳ የቱሪዝም ማዕከል እየሆነች ትገኛለች።
​ቢሾፍቱ የአፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል እንድትሆን የተሰነቀውን ራዕይ ለማሳካት የኦሮሚያ ከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ከ62,246 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የሚተገበር መዋቅራዊ ፕላን አዘጋጅቷል። ይህን ራዕይ እውን ለማድረግም ለሦስቱ የከተማዋ ክፍሎች ማለትም ለጨለለቃ፣ ለዲባዩ እና ለዱከም የአካባቢ ልማት ፕላን (LDP) ተዘጋጅቷል። በተጨማሪም እነዚህ ፕላኖች በሥራ ላይ እንዲውሉ የሚያስችል የከተማ ዲዛይን በኢንስቲትዩቱ ተነድፏል።
​በዚህም መሰረት በቢሾፍቱ አዲስ ፕላን ውስጥ፦
• ​የጨለለቃ ክፍለ ከተማ፡ የንግድ ኮሪደር፣
• ​የዱከም ክፍለ ከተማ፡ የኢንዱስትሪ እና የሎጂስቲክስ ኮሪደር፣
• ​የዲባዩ ክፍለ ከተማ፡ የዘመናዊ ግብርና ኮሪደር እንዲሆኑ ተለይቷል።
​የኦሮሚያ ከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ቢሾፍቱ በአዲሱ ፕላን እየተመራች ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለአፍሪካ ደግሞ ተመራጭ የቱሪዝም ከተማ እንድትሆን እንዲሁም መንገዶቿ የከተማዋን ውበት የሚመጥኑ እንዲሆኑ የኮሪደር ዲዛይን አዘጋጅቷል። ይህ የኮሪደር ልማት የከተማዋን የቱሪስት መስህብነት በእጅጉ ከፍ የሚያደርግ ነው።
​ባጠቃላይ የኦሮሚያ ከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ከቢሾፍቱ ከተማ የፕላን ዝግጅት፣ የከተማ ዲዛይን እና የኮሪደር ዲዛይን ያገኘውን ልምድ በመጠቀም፤ ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞችም እንደየደረጃቸውና እንዳላቸው የእድገት ዕድል የየራሳቸው ፕላን እንዲኖራቸው ሙያዊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ይህም ሁሉም የኦሮሚያ ከተሞችና የከተማ አድሳቶች የብልጽግና ማዕከል እንዲሆኑ ለማስቻል የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

Via Oromia Urban Planning Institute

@etconp

Comments

Be the first to add a comment