👉የአዲስ አበባ የመጀመሪያዎቹ ድልድዮች ታሪክ🌉🏗️

​የከተማችን የመሠረተ ልማት ታሪክ ሲነሳ ከዘመናት በፊት የተጀመሩ አበይት ሥራዎች ይታወሳሉ። ከእነዚህም መካከል የአዲስ አበባ የመጀመሪያ ድልድዮች አሠራር ይጠቀሳል፡-

​🪵 የመጀመሪያው የእንጨት ድልድይ: በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራው ድልድይ በእንጨት የተገነባ ሲሆን፣ የሰጠውም አገልግሎት አጭር ጊዜ ብቻ ነበር።

​🪨 የመጀመሪያው የድንጋይ ድልድይ (1902 ዓ.ም.): በራሺያዊ ኢንጅነር የተሠራው ይህ ድልድይ፣ አንድ ጓደኛውን የቀበና ወንዝ በመወሰዱ ምክንያት የተገነባ ነው።

በመሆኑም በምኒልክ ሆስፒታልና በራሺያ ቆንስል መካከል በሚገኘው የቀበና ወንዝ ላይ የመጀመሪያው የድንጋይ ድልድይ እውን ሆነ።

​🌉ሁለተኛው የድንጋይ ድልድይ: «የራስ መኮንን ድልድይ» በመባል የሚታወቀው ሲሆን፣ መጠሪያ ስያሜውን ያገኘው ከተሠራበት ጊዜ አንስቶ ነው።

​ምንጭ፦ አዲስ አበባ (1879-1979 ፥ ኅዳር 1979 ዓ.ም.) በዘሪሁን ጉልቴ

@etconp

Comments

Be the first to add a comment