ኢትዮጵያ ለቱርኩ ስራ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኩባንያ 213 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር እንድትከፍል ተወሰነ!

ለያፒ መርከዚ ኩባንያ እንዲከፈለው ከተወሰነለት ውስጥ 89 ሚሊዮን ዶላር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ለደረሱ ጉዳቶች የሚከፈል ነው ተብሏል።

በአዋሽ ኮምቦልቻ ወልደያ ሀራ ገበያ የባቡር መስመር ግንባታ ክርክር ጉዳይ በኢትዮጵያ እና በስራ ተቋራጩ ያፒ መርከዚ መካከል ሲካሄድ የቆየው የክስ ሂደት ተጠናቋል፡፡

ለንደን በሚገኘው የዓለም አቀፍ ግልግል ዳኝነት የተካሄደው ክርክር 392 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውን ፕሮጀክት በ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለመገንባት ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በተደረገው የስራ ውል አፈጻጸም ላይ አለመግባባት መነሳቱን ተከትሎ ነበር፡፡

ስራ ተቋራጩ ያፒ መርከዚ ኩባንያ የኢትዮጵያ መንግስት ለደረሰበት ጉዳት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ካሳ እንዲከፈለው መጠየቁን ተከትሎ ክርክሩ ሲካሄድ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ የያፒ መርከዚ ክስን ተከትሎ 400 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል ጥያቄ አቅርባ እንደነበር ካፒታል ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሰምታለች፡፡

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራር እንዳሉት ላለፉት አራት ዓመታት በለንደን ሲካሄድ የቆየው ክርክር ባሳለፍነው መስከረም 23 ቀን 2026 ተጠናቋል፡፡

በዚህ ውሳኔ መሰረትም ኢትዮጵያ ለያፒ መርከዚ የዘጠኝ በመቶ ወለድን ጨምሮ 242 ሚሊዮን ዶላር የጉዳት ካሳ እንድትከፍል ተወስኗል።

ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያ ለያፒ መርከዚ ኩባንያ በቅድመ ክፍያ መልኩ ለኩባንያው ከፍላው የነበረው 29 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር እንዲመለስላትም ተወስኗል፡፡

Via Capital

@etconp

Comments

Be the first to add a comment