በአዲስ መልክ ተዘጋጅተው የጸደቁትን የህንጻ ኮዶችና ስታንዳርዶች

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ለሀገራዊ የመሰረተ-ልማትና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ የሚታመንባቸው  ነባርና በስራ ላይ የሚገኙ የህንጻ ኮዶችና ስታንዳርዶችን የማሻሻልና የማዘመን እንዲሁም አዳዲስና አስገዳጅ ኮድና ስታንዳርዶችን የማዘጋጀት ተግባር አከናውኗል፤፡

በአዲስ መልክ ተሻሽለው የተዘጋጁት እና የጸደቁት የሕንጻ ኮዶችና ስታንዳርዶች ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ዘመኑን የሚዋጅ ብሎም ጥራት፣ ፍጥነት እና ቴክኖሎጂን ያዋሃዱ እንዲሆኑ የተቀረጹ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን መሪነትና በሀገሪቱ ከዘርፉ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው፣ በዕውቀትና በልምድ የዳበሩ ምሁራንና ባለሙያዎች ተሳታፊነት በአዲስ መልክ የተዘጋጁት ኮዶችና ስታንዳርዶች በይዘትም ሆነ ሽፋን ረገድ ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሕንጻ ኮዶችና ስታንዳርዶች የላቁ ናቸው፡፡

በአዲስ መልክ የተዘጋጁት ባለ 40 ቅጽ የህንጻ ኮድና ስታንዳርዶች ከደህንነት፣ ከዲዛይን፣ ከህንጻ መዋቅር፣ ከሕንጻ እድሳት፣ የህንጻ ከፍታ መጓጓዣ(Elevator) እና መሰል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የማሻሻያ ክለሳ ተካሂዷል፣ አዳዲስ ኮዶች እንዲሁም አስገዳጅ ማዕቀፎችም ተካተውበታል፡፡

በአዲስ መልክ ተዘጋጅተው የጸደቁት ኮዶችና ስታንዳርዶች ዝርዝር  በምስሉ የተመለከቱት ናቸው

Via ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን

🔖ለተጨማሪ የግንባታ እውቀቶች ቻናላችንን ይከታተሉ 👇

https://t.me/etconpwork

@etconp

Comments

Be the first to add a comment