​በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ስማርት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግንባታ በይፋ ተጀመረ

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ«ሰዎች ለሰዎች» ድርጅት ጋር በመተባበር በሀገራችን የመጀመሪያውን ስማርት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግንባታ በይፋ አስጀምሯል።

​የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት፤ ኮሌጁ ሲጠናቀቅ ወጣቶችን በሚከተሉት ዘመናዊ መስኮች ላይ ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን በመስጠት ብቁ እንደሚያደርግ ተመላክቷል፦

▪️​ማኑፋክቸሪንግ
▪️​አውቶሞቲቭ
▪️​ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ
​ኮሚዩኒኬሽንስ
​ቴክስታይል

​ሲኤንሲ (CNC) ቴክኖሎጂዎች
​"ሀገርን ማልማትና ከድህነት መላቀቅ በንድፈ-ሃሳብ ብቻ ስለማይቻል ሃሳብ የሚያፈልቁ አዕምሮዎችንና የሚሰሩ እጆችን ያጣመረ ክህሎት መር የሰው ሀይል አስፈላጊ ነው"-- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

​ይህ አዲስ ፕሮጀክት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ወጣቶችን ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት እንዲሁም ከንድፈ-ሃሳብ ወደ ተግባር የሚያሸጋግር ትልቅ የክህሎት ድልድይ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

​@etconp

Comments

Be the first to add a comment