በውጭ ሀገር የተሰጠ የፍርድ ቤት ውሳኔ በኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ስለሚፈፀምበት ስነስርዓት

በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጋችን በአንቀፅ 458 እንደተገለፀው በውጭ ሀገር የተሰጠ ፍርድ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊፈፀም የሚችለው
1) እንዲፈፀም የተጠየቀውን ፍርድ የወሰነው ፍርድ ቤት የሚገኝበት ሀገር በኢትዮጵያ የተሰጠውን ፍርድም የሚፈፀም መሆኑ ሲረጋገጥ
2) ፍርዱ የተሰጠው በህግ በተቋቋመ ፍ/ቤት መሆኑ ሲረጋገጥ
3) የፍርድ ባለዕዳው ቀርቦ መቃወሚያውን ለማሰማት መብት የተሰጠው መሆኑ ሲረጋገጥ
4) ፍርዱ የመጨረሻ እና ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ ሲታወቅ
5) የፍርዱ መፈፀም ለሕዝብ ሞራልና ፀጥታ ተቃራኒ ያለመሆኑ ሲታወቅ እንደሆነ ነው፡፡
እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች በአጠቃላይ መሟላት የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች በውጭ አገር የተሰጠውን ፍርድ ለማስፈፃም የሚያስችላቸው ሲሆን በተናጥል መሟላት የኢትዮጵያን ፍርድ ቤቶች በውጭ ሀገር የተሰጠውን ፍርድ ለማስፈፀም የሚያስችላቸው አይሆንም፡፡

Comments

Be the first to add a comment