ስጦታ በፍትሐብሔር ሕግ   

                  👉 የስጦታ ምንነት

   ስጦታ ማለት ሰጪው ተቀባይ ለተባለ ሌላ ሰው  ከንብረቶቹ አንዱን ያለ ዋጋ የሚለቅበት ወይም ግዴታ የሚገባበት ውል ነው። በመሆኑም ስጦታ በራሱ ውል ነው ማለት ነው።

               👉የስጦታ ልዩ ባህሪያት*

    በመርህ ደረጃ ስጦት ግላዊ ተግባር ነው ይህም ማለት ሰጪው እራሱ የሚያድረገው ተግባር ነው ማለት ነው። ስጦታ የሚደረገው በወኪሉ ሲሆን ደግሞ የሚሰጠው ንብረት አይነት እና ለማን እንደሚሰጥ በግልጽ ሊመለከት ይገባል። ስጦታ የሚደረገው የሰጪው ንብረት በሆነው ላይ ብቻ ነው።ስጦታ አድርጋለሁ ብሎ የተስፋ ቃል መስጠት በሕጉ መሠረት ግዴታን አያስከትልም ከዚህም በተጨማሪ ስጦታ ተቀባዩ ስጦታውን እቀበላለሁ በሚል ሀሳቡን መግለፅ ይኖርበታል። ስጦታ እንዲቀነስ ወይም እንዲሻር የሚቀርበው ጥያቄ ስጦታው ከተደረገበት ቀን አንስቶ እስከ ሁለት አመት ለዳኞች ካልቀረበ በቀር ዋጋ አይኖረውም።

            👉የስጦታ ሥርዓት ፎርም

     ስጦታ በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ  ወይም በሚይንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ ሊደረግ ይችላል።

*1)በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ *

    በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 881 ላይ በተደነገገው መሠረት በግልጽ ኑዛዜ ሥርዓት ፎርም መሠረት የሚፈጸም መሆኑን ሕጉ ያስረዳል። በሌላ በኩል በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ለይ የሚደረገው ስጦታ በፍ/ሕግ አንቀጽ 1723 መሠረት በጽሁፍ ሆኖ በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መሆን አለበት።

     *2) በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ*

   በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በሁለት አይነት መልኩ ሊደረግ ይችላል ይህም እጅ በእጅ በሚደረግ ማስተላለፍ ብቻ ወይም ለማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ በሚደረገው ፎርም ሊሰጥ ይችላሉ።

        👉ስጦታ ፈራሽ የሚሆንባቸው ምክንያቶች

   በሚንቀሳቀስ ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የተደረገው ስጦታ በሕጉ በተጠቀሱት  በተለያየ ምክንያቶች ፈራሽ ሊሆን የሚችሉባቸው ምክንያቶች ያሉ ሲሆን እነኚህም:-

       1ኛ የሰጪው አዕምሮ ትክክል አለመሆን

   ሰጪው ስጦታውን በሚያድርግበት ወቅት በአዕምሮ መታወክ(ህመም ምክንያት) በፍርድ የተከለከለ ሲሆን ያደረገው ስጦታ  ፈራሽ ሊሆን ይችላል ። የፍ/ሕ አንቀጽ 2437

       2ኛ ግብረ ገብነት የሌለው ወይም ሕገ-ወጥ ምክንያት ያለበት ስጦታ ፈራሽ ነው። የፍ/ሕግ አንቀጽ 2438
      
      3)በመንፈስ መጫን ምክንያት የተደረገውን ስጦታ ዳኞች ለመቀነስ ወይም ለመሻር ይችላሉ። የፍ/ሕግ አንቀጽ 2439

      4ኛ በ ፍ/ሕግ አንቀጽ 2442 ሥር በሚፈቅደው መሠረት ስጦታው የተደረገው በስህተት ወይም በተንኮል የሆነ እንደሆነ ፈራሽ ይሆናል።

  5 ስጦታ የተደረገው ክርክር ያለበት ሀብት ላይ ሲሆን ስጦታው ፈራሽ ይሆናል። የፍ/ግ አንቀጽ 2452


ፌናን ተጊበሉ
ሕዳር 14/2014 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment