ከ1997- 2007 ዓ/ም በተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የተስተዋሉ የግንባታ ጥራትና ተያያዥ ችግሮችን ለመፍታት በጥናት የተለዩ ሕንፃዎች ላይ የማስተካከያ ሥራ ሊጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
የታዩ የግንባታ ጥራትና መሰል ችግሮችን ለመለየት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ማካሄዱን ገልጿል።
በጥናቱ የችግሮቹ ዓይነትና ደረጃ ተለይቶ ቅድሚያ የእርምት ርምጃ የሚያስፈልጋቸው ሕንፃዎች ተለይተዋል። በዚህም ከነዋሪዎች ጋር በመግባባት ፣ የሥራ ተቋራጮችን በመመደብና የማስተካከያ ሥራዎችን ለመጀመር ዝግጁ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ አመልክቷል።
በተጨማሪም በጥናቱ የተመለከቱ ጉድለቶችን በተመለከተ አስፈላጊውን የሰነድና የማስረጃ ዝግጅት በማድረግ፣ በውል ግዴታ መሠረት ተጠያቂነትን ለማስፈንና ተገቢውን የሕግና የውል እርምጃ ለመውሰድ እየተሠራ መሆኑን አሳውቋል።
በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት አምስት ዓመታት የነዋሪዎችን መሰረታዊ ፍላጎትና አንገብጋቢ የሆነውን የቤት ችግር በመረዳት አዲስ የለዉጥ እሳቤን እዉን በማድረግ 496ሺ 971 ቤቶች ተገንብተዉ ለነዋሪዎች እንዲተላለፉ አድርጓል::
@etconp