👉የግንባታ ስራ ላይ የደህንነትና ጤንነት አጠባበቅ ስታንዳርድን የመተግበር አስገዳጅነት
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን (ኢኮባ) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት አዳዲሶችን ጨምሮ 48 ያህል ሀገራዊ የህንጻ ኮዶችና ስታንዳርዶችን ወደ ስራ ማስገባቱ ይታወሳል።
ከእነዚህ ውስጥ አንዱና ዋነኛው የሆነው "የግንባታ ስራ ቦታ ላይ የደህንነትና ጤንነት አጠባበቅ ስታንዳርድ" ምን እንደሚጠይቅ
እነሆ፡- ዕቅድ ማዘጋጀት፡ ማንኛውም የግንባታ ፕሮጀክት ሲጀመር የስራ ከባቢ ዕቅድ፣ የግንባታ ቦታ አቀማመጥ እና የደህንነት ዕቅድን ያካተተ ጤንነትና ደህንነት አጠባበቅ ዕቅድ መዘጋጀት አለበት።
ኃላፊ ወይም ኮሚቴ መመደብ፡ ስራ ተቋራጩ የስራ ቦታ ደህንነትን የሚከታተል ኃላፊ መመደብ ወይም የሰራተኞች ተወካይን ያካተተ ኮሚቴ ማቋቋም አለበት።
የግል መከላከያ እቃዎች፡ ሰራተኞች የስራ ቦታ ደህንነት መከላከያዎችን (PPE) በአግባቡ መጠቀማቸውን ማረጋገጥ ቀዳሚ ግዴታ ነው።
ግንዛቤና ስልጠና፡ ስለ ስራ ቦታ ደህንነት በቂ መረጃ መስጠት እና ስልጠና ማመቻቸት አማራጭ የሌለው አስገዳጅ ተግባር ነው።
ድንገተኛ አደጋ ምላሽ፡ አደጋ ሲከሰት የሚወሰዱ እርምጃዎች፣ የሚገናኙ አካላት፣ አቅራቢያ የሚገኙ የህክምና ተቋማት እና የመጓጓዣ ሁኔታዎች ግልጽ ሊሆኑ ይገባል።
⚠️ ማሳሰቢያ፡ በ2015 ዓ.ም የወጣው ደንብም ሆነ አዲሶቹ ስታንዳርዶች እንደሚደነግጉት፣ የግንባታ ቦታዎች ደኅንነታቸው የተጠበቀና በሰዎች ጤና ላይ ጉዳት የማያደርሱ መሆናቸውን ማረጋገጥ የሁሉንም የስራ ተቋራጮች ሙያዊ፣ ሰብአዊ እና ሕጋዊ ግዴታ ነው።
Via Ethio Con
@etconp