👉የግንባታ ኮንትራት ዋና ዋና ቃላትና ትርጓሜዎቻቸው በአጭሩ የሚከተሉት ናቸው:-

1. የስራ መጠን ለውጦች (Variations)

- ኦሚሽን (Omission): የታቀደ ስራ ሲቀነስ ወይም ሲሰረዝ (ዋጋ ይቀንሳል)።

- አዲሽን (Addition): አዲስ ስራ ወይም ተጨማሪ መጠን ሲጨመር (ክፍያ ይጨምራል)።

- ቫሪዬሽን ኦርደር (VO): በዲዛይን ወይም በስራ መጠን ላይ ለውጥ ለማድረግ የሚሰጥ መደበኛ ትዕዛዝ።


2. የጊዜና የክፍያ ማበረታቻዎች/ቅጣቶች

- ቦነስ (Bonus): ስራው ከቀጠሮው በፊት ሲጠናቀቅ ለኮንትራክተሩ የሚሰጥ ሽልማት።

- ፔናልቲ (Penalty/LD): ስራው በጊዜ ካልተጠናቀቀ ከኮንትራክተሩ የሚቀነስ ቅጣት።

- የጊዜ ማራዘሚያ (EOT): ከኮንትራክተሩ ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ምክንያቶች ለስራው የሚታከል ተጨማሪ ጊዜ።

- የዋጋ ለውጥ (Escalation): የጥሬ ዕቃዎች ወይም የነዳጅ ዋጋ በገበያ ላይ ሲጨምር የሚደረግ የዋጋ ማስተካከያ።

3. የክፍያ ዓይነቶችና ዋስትናዎች

- አድቫንስ (Advance): ስራ ለመጀመር ቅድሚያ የሚሰጥ ክፍያ (ከ10% - 20%)።

- ኢንተሪም ክፍያ (IPC): በየወሩ ለተከናወነ ስራ የሚከፈል ጊዜያዊ ክፍያ።

- ሪቴንሽን (Retention): ለጥራት ዋስትና ከእያንዳንዱ ክፍያ የሚቀነስ ገንዘብ (5% - 10%)።

- ፐርፎርማንስ ቦንድ: ኮንትራክተሩ ስራውን በአግባቡ ለመጨረሱ የሚይዘው የባንክ ዋስትና።

- የመጨረሻ ክፍያ (Final Payment): ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ርክክብ ሲደረግ የሚፈፀም ክፍያ።


4. ከርክክብ በኋላ ያለ ኃላፊነት

- የጉድለት ኃላፊነት ጊዜ (DLP): ስራው ካለቀ በኋላ ባሉት 6 ወይም 12 ወራት ውስጥ የሚታዩ ብልሽቶች ኮንትራክተሩ በነፃ የሚያስተካክልበት ጊዜ።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment