👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ዛሬ ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ስራ አስጀመሩ።

🚧ስለ ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ምን ያህል ያውቃሉ?

💫የመጀመሪያው ምዕራፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሥራ በአመት 60 ሚሊዮን ተጓዦችን የማስተናገድ አቅም አለዉ

💫ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ 40 ኪሎሜትር አካባቢ በምትገኘውና 1910 ሜትር ከፍታ ባላት ቢሾፍቱ ከተማ ይገነባል

💫ግንባታዉ ሲጠናቀቅ አፍሪካን ከአለም ቀዳሚ የአየር ትራንስፖርት መነኻሪያዎች አንዷ ያደርጋታል

💫ሃገሪቱ በአመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ላይ እንድትደርስ ያደርጋል

💫ቢሾፍቱ ለአውሮፕላኖች ሥራ የተመቸ ከባቢ አላት

💫መዳረሻቸውን ኢትዮጵያ ላደረጉም ሆነ ለትራንዚት መንገደኞች ብቁ ሁኔታ ያላት ከተማ ናት

💫በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ይሆናል

💫ከነባሩ የአየር ትራንስፖርት ምኅዳር ጋር በቀላሉ የተዋሃደ አሠራር እንዲኖር ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል

💫ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ 25 ሚሊዮን የሚጠጉ መንገደኞችን በአመት የማስተናገድ አቅሙ አለዉ

💫ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግምባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ አላማን ያነገበ ነው

💫ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ የኢንደስትሪ ማስፋፊያ አጀንዳ እና የረጅም ዘመን የአቪየሽን ስትራቴጂ ጋር የተናበበ ነው

💫ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያጠናክራል

💫በAfCFTA ማህቀፍ የአፍሪካን የማገናኘት አቅም ይጨምራል

💫የንግድ እና ቱሪዝም ኮሪደሮችን ያሰፋል

💫ኢትዮጵያንም ቀዳሚ የበይነ አኅጉር ማዕከል ያደርጋታል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment