👉የስላብ ብረት (Slab Rebar Work) በሚታሰርበት ወቅት ሊደረጉ የሚገቡ ዋና ዋና ጥንቃቄዎች!

​የስላብ ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት የብረት ማሰር ስራው በህንፃው ጥንካሬ እና ደህንነት ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አለው።

🌟በሳይት ላይ የቁጥጥር ስራ ስናደርግ ትኩረት ልንሰጣቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​1️⃣ Spacer Blocks (ኮንክሪት ከቨር): ብረቶቹ ከፎርምወርክ (Formwork) እንጨት ጋር እንዳይነካኩ እና ከስር በቂ የኮንክሪት ሽፋን (Concrete Cover) እንዲኖራቸው ኮንክሪት ወይም ፕላስቲክ ስፔሰሮችን መጠቀም።

​2️⃣ Bar Spacing & Overlap (የብረት ርቀት እና ማያያዣ): በዲዛይኑ መሰረት በብረቶች መካከል ያለው ርቀት (Spacing) በትክክል መጠበቁን እና የብረት ማያያዣ (Lap Length) ርዝመት በቂ መሆኑን ማረጋገጥ።

​3️⃣ Binding Wire (የማሰሪያ ቢያንኮ): እያንዳንዱ የብረት መገናኛ (Intersection) በሚገባ በማሰሪያ ቢያንኮ መታሰሩን ማረጋገጥ—ኮንክሪት ሲሞላ ብረቱ ቦታውን እንዳይቀይር።

​4️⃣ Top & Bottom Mesh (የላይኛ እና የታችኛ ብረት): ድብል ሜሽ (Double Mesh) በሚሆንበት ጊዜ በሁለቱ ሜሾች መካከል ያለው ርቀት እንዳይጠበብ ወንበር/ቼር (Chairs) መጠቀም።

​5️⃣ የፅዳት ስራ (Site Cleaning): ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት በፖሊቲን/ፕላስቲክ (Polythene sheet) ላይ ያሉ የዛፍ ቅጠሎች፣ የቢያንኮ ቁራጮች እና አቧራዎች በሚገባ መጽዳት አለባቸው።

🚥​ተመሳሳይ ሙያዊ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የ YouTube ገጻችንን Subscribe ያድርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp

Comments

Be the first to add a comment