የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ጤና ይስጥልኝ!
የመንግስት መ/ቤቶችን ማህተሞች ወደ ሀሰተኛነት መለወጥ ወይም በማህተሞቹ ያለአግባብ መገልገል በጽኑ እስራት የሚያስቀጣ የወንጀል ድርጊት መሆኑን ያውቃሉ?
በወንጀል ህግ አንቀጽ 363 መሰረት፥-
1. ማንም ሰው፡-
ሀ) ለመንግስት ስራ ጉዳይ ብቻ በሚታተም የመንግስት ወይም ከመንግስት አካላት በአንዱ ማህተም ወይም ወደ ሀሰተኛነት በተለወጠ ወይም መስሎ በተሰራ ማህተም የተገለገለ እንደሆነ፤ ወይም
ለ) በእውነተኛው ማህተም ያላግባብ የሰራበት እንደሆነ
ከሶስት ዓመት እስከ አስር ዓመት ሊደርስ በሚችል ፅኑ እስራት ይቀጣል።
2. ይህ የወንጀል ድርጊት በሀገር ጥቅም ወይም መብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰ ከአምስት ዓመት እስከ ሀያ ዓመት ሊደርስ በሚችል ፅኑ እስራት ይቀጣል።
በቦሌ ክ/ከተማ የፍትህ ጽ/ቤት በህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
ፋሲካ አጌና (ዐቃቤ ህግ)
ሚያዝያ 2014ዓ.ም
Comments
Be the first to add a comment