ክፍል 2
…… ከህጻናት መብት የቀጠለ…
ሃገራችን ኢትዮጵያም የህጻናት መብት ኮንቬንሽንን ከፈረሙ ሃገራት መካከል በመሆኗ አገሪቱ በምትተዳደርበት የኢትጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት በአንቀጽ 9 (4) ያጸደቀቻቸዉን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ሕግ አካል ከማድረግ ባለፈ የሕጻናት መብት በዚሁ ሕግ ጥበቃ ተደርጎለታል፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት
አንቀጽ 36 የሕጻናት መብት (1) ማንኛዉም ህጻን የሚከተሉት መብቶች አሉት፡-
ሀ) በሕይወት የመኖር
ለ)ስምና ዜግነት የማግኘት
ሐ) በዋጆቹን ወይም በሕግ የማሳደግ መብት ያላቸዉን ሰዎች የማወቅና የእነሱንም እንክብካቤ የማግኘት
መ)ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ በትምህርቱ በጤናዉና በደህንነቱ ላይ ጉዳት ሚያደርሱ ሥራዎች እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ
ሠ) በትምህርት ቤቶች ወይም በሕጻናት ማሳደጊያ ተቋሞች ዉስጥ በአካሉ ከሚፈጸም ወይም ከጭካኔና ኢሰብዓዊ ከሆነ ቅጣት ነፃ የመሆን
አንቀጽ 36 የሕጻናት መብት (2) ሕጻናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰዱበት ጊዜ በመንግሥታዊ ወይም በግል የበጎ አድራጎት ተቋሞች በፍ/ቤቶች በአስተዳደር ባለሥልጣኖች ወይም በሕግ አዉጪ አካላት የሕጻናት ደህንነት በቀደምትነት መታሰብ አለበት
አንቀጽ 36 የሕጻናት መብት (3) ወጣት አጥፊዎች በማረሚያ ወይም በመቋቋሚያ ተቋሞች የሚገኙ በመንግሥት እርዳታ የሚያድጉ ወጣቶች በመንግሥት ወይም በግል እጓለ ማዉታን ተቋሞች ዉስጥ የሚገኙ ወጣቶች ከአዋቂዎች ተለይተዉ መያዝ አለባቸዉ፡፡
አንቀጽ 36 የሕጻናት መብት (4) ከጋብቻ ዉጭ የተወለዱ ህጻናት በጋብቻ ከተወለዱ ሕጻናት ጋር እኩል መብት አላቸዉ
አንቀጽ 36 የሕጻናት መብት (5) መንግሥት ለእጓለ ማዉታን ልዩ ጥበቃ ያደርግላቸዋል፡፡ በጉዲፈቻ የሚያድጉበትን ሥርዓት የሚያመቻቹና የሚያራምዱ ተቋሞች እንዲመሰረቱ ያበረታታል፡፡
ህድአት ጌታቸዉ ሰኔ/2013 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment