የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይህን ድንጋጌ መሠረት በማድረግ በፊቱ በቀረቡ በርካታ ጉዳዮች ላይ በውርስ ይርጋ ላይ
በርካታ የሕግ ትርጉም ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
➢ በሰ.መ.ቁ 25664 በሰጠው ውሳኔ ወራሽ የሆነ ሰው የውርስ ንብረቱን ለማስመለስ ወራሽ ባልሆነ ሰው ላይ የሚያቀርበው ክስ
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677 እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 1845 መሠረት በ10 ዓመት ይርጋ የሚታገድ ነው በሚል ወስኗል፡፡
➢ በሰ.መ.ቁ 44025 በሰጠው ውሳኔ ወራሾች በጋራ ይዘው ሲያስተዳድሩት ወይም ሲጠቀሙበት የነበረ የውርስ ንብረት ለመጠየቅ
የቀረበ ክስ ላይ የቀረበ የይርጋ መቃወሚያ ተቀባይነት የሌለው ነው በሚል ወስኗል፡፡
➢ በሰ.መ.ቁ 120841 በሰጠው ውሳኔ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ወራሽነት መብቱን ለአካለ መጠን ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ
15 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ የውርሱን ንብረት ለመጠየቅ በይርጋ አይታገድም በሚል ወስኗል፡፡ ይህ ውሳኔ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 198
እና 100(2) ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ የተሰጠ ውሳኔ ነው፡፡
➢ በሰ.መ.ቁ 224271 ጥቅምት 02 ቀን 2015 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፡- በሰ.መ.ቁ 171038 ወራሽ በሆነ እና ወራሽ ባልሆነ ሰው
መካከል ላለ የውርስ ንብረት ክርክር ተፈጻሚነት ያለው የ10 አመት ይርጋ እንደሆነ ይህ የአስር አመቱ የይርጋ ግዜ መቆጠር
ያለበት አካለመጠን ያላደረሰ ሰው አካለመጠን ካደረሰበት ግዜ አንስቶ መሆኑን፤ የመዝገቡ ተጠሪ አካለመጠን ካደረሰችበት ጊዜ
ጀምሮ ክስ እስካቀረበችበት ቀን ድረስ ያለው ጊዜ ሲታሰብ 10(አስር) አመት ያለፈው መሆኑን፤ ምንም እንኳ የወረዳው ፍርድ
ቤት የተጠሪን ክስ በይርጋ ቀሪ ሲያደርግ የ15 አመት ይርጋን መሰረት ማድረጉ አግባብ ባይሆንም ክሱ በይርጋ ቀሪ መደረጉ
ተገቢ ነው ሲል ወስኗል፡፡
➢ በሰ.መ.ቁ 44612 በሰጠው ውሳኔ የወራሽነት መብትን በሕግ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ያረጋገጡ ወራሾች የውርስ ንብረት
ክፍፍልን ማቅረብ ጥያቄ በማናቸውም ጊዜ ማቅረብ ይችላሉ በሚል ወስኗል
➢ በሰ.መ.ቁ 243973 ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በ7 ዳኞች የተሰጠ ውሳኔ፡- በፍ/ሕ/ቁ. 1000 የተመለከተውን
የይርጋ ጊዜ ከወራሽነት የምስክር ወረቀት ጋር በማያያዝ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ መብቱን የሚያስከብር ሰው
የንብረት ጥያቄ ለማቅረብ ገደብ የሌለበት ተደርጎ የተሰጡ ውሳኔዎች አሉ፡፡ ይህን አቋም ለመፈተሽና ለተያዘውም
ጭብጥ ግልጽነት እንዲረዳ የወራሽነት የምስክር ወረቀትና የወራሽነት ጥያቄ ያላቸውን መስተጋብር ግልጽ ማድረግ
ይገባል፡፡ ሁለቱም ሐሳቦችን የያዙት ድንጋጌዎች በሕግ መድብሉ አንድ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የይርጋ ጊዜው
የተነሳው ግን ከወራሽነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ በአጠቃለይ የወራሽነት የምስክር ወረቀትን በተመለከተ
በተጠቀሰው በሕግ መድብሉ ክፍል የተደነገገ የይርጋ ገደብ የለም፡፡ አንቀጽ 1000 በግልጽ የሚናገረው የወራሽነት
ጥያቄ ተቀባይነት የማያገኝበትን ጊዜ ነው፡፡ ጊዜው ተፈጻሚ የሚሆንበትን ሁኔታ የበለጠ ግልጽ ለማድረግ የወራሽነት
ጥያቄ ከወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዲሰጠ ከሚቀርብ ማመልከቻ ያለውን ልዩነት ማየት ተገቢ ነው፡፡ የወራሽነት
የምስክር ወረቀት ስሙ እንደሚናገረው የምስክር ወረቀት ሲሆን በተግባር የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰ/መ/ቁ. 243973 ፍርድ ቤቶች አንድ ሰው ከሟች
ጋር ባለው ዝምድና ወይም በኑዛዜ መነሻነት ወራሽ መሆኑን በማረጋገጥ የሚሰጡት ውሳኔ ነው፡፡ ይህ ማስረጃ የህግ
ሁኔታን የሚያረጋግጥ በውጤቱም ሕጉ የሚወሰደውን ግምት የሚያረጋግጥ እንጂ በተከራካሪ ወገኖች መካከል ላለ
ክርክር መፍትሔ የሚሰጥ አይደለም፡፡
የወራሽነት ጥያቄ (petitio hereditatis) ጥንታዊ ጽንሰ ሐሳብ ሲሆን አንድ ሰው ከሟች ንብረት ለመውረስ
የሚያቀርበው ክስ ነው፡፡ የፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 999 እንደሚያስቀምጠው ደግሞ አንድ ሰው ወራሽነ

Comments

Be the first to add a comment