👉ከግንባታ ህጎች አንጻር እንዴት ያዩታል?
(ቅሬታ የተፈጠረበት እውነተኛ - Case 1)

📌አንድ የመንግሥት ተቋም ሕንፃ ለማስገንባት ከተቋራጩ ጋር ውል ተፈራረመ።

⏺ተቋራጩ ሥራውን ከጀመረ በኋላ በተሰጠው ዲዛይን (Drawing) መሰረት ልኬት እየፈጸመ የአሠሪው ተቋም አማካሪ መሐንዲስ (Engineer) እያጸደቀለት ቢሠራም በእውነተኛው ሥራው ላይ ያለው የተመዘገበው የሥራ መጠን (Actual Quantity of activities) በውል ሰነዱ ላይ ከተፈራረሙበት የሥራ መጠን (with the quantities specified in the BOQ of contract document) በ49 በመቶ (49%) ጭማሪ ተገኘበት።

▶️በዚህ መካከል ተቋራጩ በእውነተኛው የሥራ መጠን ተባዝቶ ክፍያ እንዲፈጸምለት ጠየቀ። አሰሪው መሥሪያ ቤት ተጨማሪ የመጣበትን ጉዳይ በውል ስምምነቱ ሰነድ ላይ ከተገለጸው በላይ ስለሆነ ክፍያ አልፈጽምም ብሎ የግንባታ ሂደቱ እንዲቆም ትዕዛዝ ሰጠ።

💫ይህ የክፍያ ጉዳይ፦

⭐️1ኛ. ከግንባታ ህግ አንጻር ተገቢነት ያለው ማንኛው ወገን ነው?

⭐️2ኛ. ጥፋት ያለበት ባለድርሻ አካል ማነው? ምን አይነት ጥፋት?

📜መልሱን በዚሁ ገጽ እንለቃቀን...

📩ከዚያ በፊት ግን ሁላችንም ምላሽ በመስጠት ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪያችን ዕድገት እውቀት እየተጋራን አስተዋጽኦ እንክፈል።

🔏ሀሳብ እና አስታያየታቹ Comment Box ወይም መወያያ ግሩፓችን @COTMp ይፃፉልን🙏

@etconp

6 comments

አማካሪ መሀንድሱ ካረጋገጠለት ተቋራጩ የሰራውን ስራ ክፍያ መጠየቅ መብት አለው።ጥፋተኛው አማካሪ መሀንድሱ ነው።የስራ ልዩነት ካለ ባለቤቱ እንድያውቀው አድርጎ ነበር ለኮንትራክተሩ እንድሰራ መፍቀድ የነበረበት
seid Habesha
በመጀመሪያ ደረጃ የሚዳኛቸዉ የግንባታ ዉሉ ነዉ ይሄ ብዙ ዝርዝር ሰነዶች ይኖሩታል ሲቀጥል አማካሪዉ የድዛይን ለወጥ መኖሩን ለስራው ባለቤት በሰነድ ካሳወቀ እና የማሳወቅም ግዴታ ስላለበት የስራ ተቋራጩ በፀደቀ ድዛይን ከሰራ ከነ ኪሳራዉ አሰሪዉ የመክፈል ግዴታ አለበት አማራ ክልል መገጭ ግድብ ፕሮጀክት እንደሆነዉ ማለት ነዉ
governed by SCC which is Varation exceed 30% so what?
በመጀመሪያ አማካሪ መሀንዲሱ ዲዛይን ሪቨዠን ሰርቶ የ ኳንቲቲም የሁን ዲዛይን ለውጥ ካለ ለባለቤቱ አሳውቆ ማፀደቅ ነበረበት።ሲቀጥል ተቋራጩ ከባለቤቱ ተፈራርሞ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት በአማካሪ መሀንዲሱ እያፀደቀ እስከሰራ ድረስ ክፍያው ሊከፈለው ይገባል።በተጨማሪም ጭማሪው 25%በላይ ስለሆነ የ ነጠላ ዋጋ ማሻሻያም ክሌም የማረግ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Kebede Indris
አማካሪ መሃንዲሱ በፅሁፍ ትዕዛዝ እየሠጠዉ የሠራ ከሆነ ክፍያዉ ይከፈለዋል። በህጋችን እስከ 30% ስራ መጨመርም መቀነስም ይቻላል። ከ30% በላይ ከሆነ ተጨማሪ ዉል ያስፈልገዋል። ይህ ሳይፈፀም ከቀረ የአማካሪ መሃንዲስ ስህተት ቢሆንም ኮንትራክተሩ ለሠራዉ ስራ በፅሁፍ ትዕዛዝ ተቀብሎ ከሠራ (በፅሁፍ የተሠጠ ትዕዛዝ የዉሉ አካል ስለሚሆን) ሊከፈለዉ ይገባል ባይ ነኝ።
ጥያቄው ግልፅ አይደለም!
ውሉ ሲያዝ በምን አይነት የውል አስተዳደር እንደሚመራ ግልፅ አድርገው!
የተለያዩ ህጎች ስላሉ!
ለምሳሌ. FPPA, World bank GCC, ...?
ለማንኛውም በ25/1% በሚለው ህግ ውል ተይዞ ከሆነ እንኳን ለሰራው ስራ በውሉ ባለው መስሪያ ዋጋ እንዲያውም በወቅታዊ የገበያ ዋጋ ነው የሚከፈለው።
እዚህ ላይ አማካሪው ከ15% በላይ ስልጣን የለውም።

በሌላ ህግ ደግሞ አጠቃላይ ስራው ከ 30% በላይ በማይበልጥ ሁኔታ የተጨማሪ ስራው ይፀድቃል።

አማካሪ መሃንዲሱ የፕሮጀክቱን ባለቤት አሳውቆ በጀት ሳይዝ ይህን ስራ ማሰራት የለበትም።
ሲቀጥል ደግሞ ኮንትራክተሩ ከውል ውስጥ ያለ ስራ ቢሆንም የዚህ ስራ የስራ መጠን ከጠቅላላ የፕሮጀክት ዋጋ አንፃር ሳያይ ዝም ብሎ መስራቱ አግባብነት የሌለው ነው።

ተጠያቂነትን በሚመለከት
- ዲዛይኑን የሰራው እና ያጫረተው አማካሪው ከሆነ ይህ አማካሪ በፍፁም ተጠያቂ ነው። ሲቀጥል ባለቤት ከዛ ስራ ተቋራጭ በተዋረድ።
- ዲዛይኑን ሌላ አማካሪ ሰርቶት እሱ ለማማከር ብቻ ገብቶ ከሆነ የመጀመሪያ ተጠያቂው ባለቤቱ ሲሆን ቀጣይ እሱ ይሆናል። ከዛ ስራ ተቋራጩ።
በነገራችን ላይ ጨረታው ሲወጣ ሆን ብለው የቀነሱት የስራ መጠን ሊሆንም ይችላል። ስራ ተቋራጩ ዋጋውን ትልቅ አድርጎ እንዲገባ ተመሳጥረውም ሊሆን ይችላል።

አጠቃላይ በቅደም ተከተል ተጠያቂዎቹ
- አማካሪ - ስራ ተቋራጭ - ባለቤት

እዚህ ላይ ባለቤት ባለሙያ ከሌለው ነው!

አሰሪ ባለቤቱ ባለሙያ ያለው ተቋም ከሆነ
- አማካሪ - ባለቤት - ተቋራጭ