👉የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በአሁኑ ሰዓት በአዳማ ከተማ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

📜ውይይት እየተካሄደ ያለባቸው ርዕሰ ጉዳዮች:-

▪️ ረቂቅ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ አዋጅ፣

▪️የኮንስትራክሽን የብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ ማሻሻያ እና

▪️ረቂቅ የኮንስትራክሽን የቁጥጥር መመሪያ  ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

📩ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እየቀረቡ ባሉት ሰነዶች ላይ የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትን እንዲሁም ጥያቄም ካላችሁ እዚሁ ላይ አስቀምጡልን።

💫ባለሙያ ጋብዘን ምላሽ የምንሰጥበት ይሆናል።

@etconp

3 comments

ልምድና ችሎታ መታየት አለበት ኮንስትራክሽን ቤተሰብ ያልሆነ በአጋጣሚ ወደ እንዱስትሪው የገቡ ባለሐብቶች እንደፈለጉ የሚያምሱት ሆኗል በቂ የትምሕርት ማስረጃና የስራ ልምድ ያለው እያለ ምንም እውቀት ና ስራው ልምድ የሌለው እንደስትሪውን ተቆጣጥረውታል ባለሙያናልምድ ባለው ሠራተኛ ቢመራ ጥሩ እድገት የሚገኝ ይሆናል።
Zemen. T
የአንድ ፕሮጀክት ባለቤት በሚያሰራው ፕሮጀክት ላይ የቴክኒካል ስራዎች ላይ ያለው ገደብ እስከምን ድረስ ነው?
የኮንስትራክሽን ባለስልጣኑ በሚያወጣቸው መመሪያዎች እና ህጎች መሰረት አንድ ባለሙያ ስራውን ሲያሰራ ባለቤቱ ጣልቃ በመግባት እኔ ባልሁት ይሰራልኝ ሀላፊነቱን እኔው እወስዳለሁ በሚል ባለሙያው ላይ ከፍተኛ ጫና ሲያደርግ ይስተዋላል።

የኮንስትራክሽን ባለስልጣኑ መመሪያ እና ህግ ብዙ ግዜ ሲያወጣ ለስራ ተቋራጩ እና አማካሪው ነው።ነገር ግን በፕሮጀክት ባለቤት ላይም ጠንከር ያለ ህግ እና መመሪያ ቢወጣ ባለስልጣኑ የሚያወጣቸው የፕሮጀክት ህግ እና መመሪያዎች ሳይሸራረፉ መተግበር ይችላሉ ባይ ነኝ።ባለሙያውም ትክክለኛ እውቀቱን ተጠቅሞ የኮንስትራክሽን ህግ እና መመሪያዎችን በአግባቡ ተግብሮ መስራት ሚችልበትን ሁኔታ በእጅጉ ያሰፋለታል።

ስለዚህ በፕሮጀክት ባለቤት ላይ ትክክለኛ ህግ ሊወጣ ይገባል።
Agizew
ውሎች ለኮንትራክተርም መብት በግልፅ ቢቀመጥና ለክላይት ብቻ ያጋደለ ባይሆን ጨረታዎች ፍትሐዊና አሳታፊ ለኦዲት ታይታ ብቻ ሳይሆን ግልፅ ቢሆኑ ብዙ ልምድ ያላቸው ስራ ተቋራጮች ከፍተኛ ስራ አልሰራችሁም ተብሎ ከኮንስትራክሽን ኤንዳስትሪው ሆን ተብሎ ሒድ አትበለው አካሔድ በግልፅ ቢታይ