⚖️ የፍርድ ቤት መጥሪያ በ Telegram (ማህበራዊ ሚዲያ) ሊደርስ ይችላል?
Abrham Yohanes
የሰበር መዝገብ ቁጥር: 213020 ቀን: 🗓 ሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም

📰 የጉዳዩ ማጠቃለያ
የጉዳዩ ክርክር የተጀመረው በአሁን ተጠሪ (ወ/ሮ ዓለም ቤዛ የሻው) በአሁን አመልካች (አቶ ዳኛቸው ደመቀ ከበደ) ላይ ባቀረቡት የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል እና የልጅ ቀለብ ጥያቄ ነው። ግራ ቀኙ ለ10 ዓመታት ያህል በጋብቻ ሳይተሳሰሩ አብረው የኖሩ ሲሆን፣ በተፈራው የጋራ ቤት 🏠 ላይ ክፍፍል እና ለልጃቸው ቀለብ 💰 እንዲቆረጥ ተጠይቋል።
የሥር ፍርድ ቤት (የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት) መጥሪያውን ለአመልካች ለማድረስ የተለያዩ ሙከራዎችን (ፖሊስን ማዘዝ 👮‍♂️፣ በጋዜጣ ጥሪ 📢 ማድረግ) አድርጓል፤ ምክንያቱም ተጠሪ አመልካች አገር ውስጥ እንደሌለ ገልጻለች። ፍርድ ቤቱ አመልካች በጋዜጣ ጥሪ ቀርቦ ባለማግኘቱ በሌለበት ጉዳዩን አይቶ ቤቱን ለጋራ ሀብትነት ወስኖ የልጅ ቀለብ በወር 3,000 ብር እንዲከፍል ወስኗል።
አመልካች (አቶ ዳኛቸው) ከኢትዮጵያ ውጭ (እንግሊዝ 🇬🇧) ነዋሪ መሆናቸውን በመግለጽ፣ የፍርድ ቤቱ መጥሪያ በአግባቡ ሳይደርሳቸው በሌሉበት የተሰጠው ውሳኔ እንዲነሳላቸው በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 78 መሰረት አቤቱታ አቅርበዋል። ምክንያታቸውም ውሳኔውን ያወቁት ተጠሪ በስልክ 📞 ደውላ በቫይበር 📲 ከላከችላቸው በኋላ መሆኑን እና ከእኔ ጋር በስልክና በቫይቨር እንገናኝ የነበረ ሲሆን፣ ዉሳኔዉን ስልክ ደዉላልኝና በቫይቨር እንደላከችልኝ ሁሉ፣ ክሱን በቫይቨር ወይም በቴሌግራም 💬 ልታሳዉቀኝ እየቻለች የአመልካችን አድራሻ አላዉቀዉም በማለት በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግ ማድረጓ ከቅን ልቦና 😇 ዉጭ በመሆኑ ፍትሕ የመግኘት መብታቸው እንደተነገፈ በአቤቱታቸው ገልጸዋል።
የሥር ፍርድ ቤት የአመልካቹን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ውሳኔውን አፅንቷል። ይግባኙ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አፅንቶታል። በመጨረሻም አመልካች ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ❌ ተፈጽሞበታል በማለት ለሰበር ሰሚ ችሎት 🏛 አቤቱታ አቅርበዋል።

📜 የሕግ ትርጉም
ችሎቱ የመጥሪያ አደራረስ ሥርዓትን በሚመለከት በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 94-110 ያሉትን ድንጋጌዎች ተመልክቷል።
•  የመጥሪያ አደራረስ ቅደም ተከተል: የመጥሪያ አደራረስ ሂደት አራት የቅደም ተከተል ደረጃዎች እንዳሉት ተንትኗል። እነርሱም፡- ለተከሳሽ ለራሱ ማድረስ፣ መጥሪያውን ሊያደርስ ለሚችል ሰው ማድረስ፣ በፖስታ ✉️ ማድረስ፣ በመጨረሻም ምትክ የመጥሪያ አደራረስ ዘዴን (እንደ ጋዜጣ) መጠቀም ናቸው።

•  የፍርድ ቤቱ ግዴታ: ፍርድ ቤት ክስ የቀረበበት ወገን የመከላከልና የመከራከር ሕገ መንግስታዊ መብት 🗣 እንዳይነፈግ፣ ሕጉ በዘረጋው የመጥሪያ አደራረስ ዘዴዎች ቅደም ተከተል መሰረት በተሻለ አማራጭ መጥሪያው እንዲደርስ ጥረት ማድረግ ይገባዋል።

•  በጉዳዩ ላይ ያለው ትርጓሜ: የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር በስልክና በቴሌግራም ግንኙነት እንዳላት ለፍርድ ቤቱ ሳታሳውቅ ቀርታ፣ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻው አማራጭ የሆነውን በጋዜጣ የመጥራት ዘዴን ወዲያውኑ መጠቀም ተገቢ አልነበረም። ፍርድ ቤቱ የተሻለ አማራጭ የመጥሪያ ዘዴ (ለምሳሌ ተጠሪ በስልክና በቴሌግራም ግንኙነት መኖሩን አስመልክቶ ማሳወቅ ወይም መጥሪያ በፖስታ ለመላክ መሞከር) ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ሳያደርግ በሌለበት ውሳኔ መስጠቱ ፍትሓዊ ሙግት የመስማት ሂደት እና የመሰማት መብትን የነፈገ ነው ብሏል።

•  ችሎቱ በሰ.መ.ቁ. 53113 (ቅጽ 12) ላይ የተላለፈውን አስገዳጅ ውሳኔ ✅ ተፈጻሚነት እንዳለው አረጋግጧል።

Comments

Be the first to add a comment