ጤና ይስጥልኝ
ከዚህ ቀደም በ“የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ ቁጥር 1100/2011 " ድንጋጌ ላይ በመነሳት በሠራዊቱ ዉስጥ አንዳንድ ጥቅማ ጥቅሞችን በማሳየት በአዋጁ ላይ ስለተቀመጡት የማዕረግ ደረጃዎች እና ስለሚሰጡ ሽልማቶች ጽሑፍ እንደምናቀርብ ቃል በገባነዉ መሠረት፤ አነሆ፡-
መልካም ንባብ፡-
የመከላከያ ሠራዊት በምድር፤ በአየር፤ በባህር ኃይል እና በልዩ ዘመቻዎች ኃይል የሚደራጅ ሆኖ እንደአስፈላጊነትም የስፔስና የሳይበር ኃይሎችን ሊያካትት እንደሚችል የተደነገገዉ ቢኖርም በአዋጁ ላይ የማዕረግ ደረጃዎቻቸዉ ተዘርዝሮ የምናገኘዉ የምድር እና የአየር ኃይልን በመሆኑ ይህንኑ እንደሚከተለዉ እናሰፍረዋለን፡-
የማዕረግ ደረጃዎች
በምድር ኃይል
ሀ) ምክትል አስር አለቃ ቸ) ምክትል መቶ አለቃ
ለ) አስር አለቃ ኀ) መቶ አለቃ
ሐ) ሃምሳ አለቃ ነ) ሻምበል
መ) መጋቢ ሃምሳ አለቃ ኘ) ሻለቃ
ሠ) ሻምበል ባሻ አ) ሌተናል ኮሎኔል
ረ) ሻለቃ መጋቢ ባሻ ከ) ኮሎኔል
ሰ) ሻለቃ ባሻ ኸ)ብርጋዴር ጀነራል
ሸ) ጁኒየር ዋራንት ኦፊሰር ወ)ሜጀር ጀነራል
ቀ) ሲኒየር ዋራንት ሶፊሰር ዐ) ሌተናል ጀነራል
በ) ማስተር ዋራንት ኦፊሰር ዘ) ጀነራል
ተ) ቺፍ ዋራንት ኦፊሰር
በአየር ኃይል
በአየር ኃይል የማዕረግ ደረጃዎች ከጁኒየር ዋራንት ኦፊሰር እስከ ጀነራል ድረስ ያሉት (ከፊደል ሸ እስከ ፊደል ዘ) ተመሳሳይ ሆነዉ ከጀነራል ዋራንት ኦፊሰር በታች ያሉት የአየር ኃይል የማዕረግ ደረጃዎች የሚከተለዉ ይሆናል፡-
ደረጀ ማርቆስ ጥር 2013 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment