የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከIFC ጋር በገባው ውል መሰረት የቤት መግዣና መስሪያ ብድር መልሶ ማቋቋሚያ ተቋም ይቋቋማል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ ተቋሙ ባንኮች በያመቱ ለቤት የሚሰጡትን ብድር ከስር ከስር ለመተካት በትሪሊዮን የሚቆጠር ብር ያስፈልገዋል፡፡
ለዚህም የጡረታ ፈንዶች መዋቅራዊ ማሻሻያ ያስልጋቸዋል እየተባለ ነው፡፡
የጡረታ ፈንዶች እና ሌሎችን ዘዴዎች በመጠቀም የሚቋቋመው የቤት ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ተቋም ጥሬ ገንዘብ ይሰበስባል ተብሏል፡፡
ይሁንና በቀደመው አሰራር መንግስት ከፍተኛውን የጡረታ ፈንድ በአንድ ነጥብ አምስት በመቶ ወለድ በመንግስት የግምጃ ቤት ሰነድ በመበደር የበጀት ማሟያ ሲያደርገው ቆይቷል፡፡
አሁን ባለው አሰራርም በግምጃ ቤት ሰነድ ከፈንዱ ብድር ሲወስድ በአማካይ ወለዱ 6 በመቶ ድረስ ብቻ ነው፡፡
በመሆኑም የጡረታ ፈንዶች ብር እያገኙ ሳይሆን እየከሰሩ መሆኑን በፋይናንስ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
የጡረታ ፈንዶች ለቤት ግዥ መልሶ ማጠናከሪያ ተቋሙ የተሻለ የጥሬ ገንዘብ ምንጭ እንዲሆኑ ካስፈለገ መዋቅራዊ ማሻሻያ በማድረግ ተጠሪነታቸው ከብሔራዊ ባንክ ወጥቶ ራሱን የቻለ ተቆጣጣሪ ተቋም ያስፈልጋቸዋል ተብሏል፡፡
በዚህም የሚያገኙት ወለድ ገበያ ተኮር እንዲሆን ማድረግና የሚሰበሰበው የጡረታ ፈንድም አሁን ካለው አነስተኛ መጠን የሰፋ እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ሸገር ያነጋገራቸው የፕራግማ ካፒታል መስራችና የፋይናንስ ባለሙያው አቶ መርዕድ ፍቅረዮሀንስ መክረዋል፡፡
Via Sheger FM
@etconp