🚧የትራፊክ ማስታወቂያ

ከመርካቶ–መሳለሚያ ወደ 18 ቁጥር ማዞሪያ የሚወስደውን መንገድ ከሚያካሂደው ግንባታ ጋር ተያይዞ፣ የ18 ቁጥር ማዞሪያ የቀለበት መንገድ ከመስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለጊዜው ዝግ ይሆናል ብሏል።

🔹 የከባድ ተሽከርካሪዎች በተዘጋጀላቸው አማራጭ መንገዶች እንዲጓዙ ተመላክቷል። ከአዲሱ ገበያ/ሸጎሌ ወደ 18 ማዞሪያ እና ጦር ኃይሎች የሚጓዙ ከባድ መኪኖች የዊንጌት አደባባይ ላይኛውን ድልድይ መጠቀም አይፈቀድላቸውም።

🔹 ቀላልና መካከለኛ ተሽከርካሪዎች ደግሞ በመሳለሚያ፣ አጠና ተራ፣ ዊንጌት፣ ኮልፌ ፓርክ እና ሌሎች የውስጥ አማራጭ መንገዶች በመጠቀም መድረሻቸውን እንዲያደርሱ ተመላክቷል።

🔹 ከአሸዋ ሜዳ/ቡራዩ ወደ ዊንጌት የሚጓዙ ከባድ መኪኖች የተጨማሪ የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ አማራጭ መስመሮችን እንዲጠቀሙ ተመክረዋል።

⚠️ማሳሰቢያ፦ በአማራጭ የትራፊክ መስመሮች ላይ ትራፊክን የሚያውክ መኪና ማቆም የተከለከለ ሲሆን፣ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ምልክቶችንና የትራፊክ ፖሊስ/አስተባባሪዎችን መመሪያ እንዲከተሉ ተጠይቀዋል።

📌 መንገዱ መዘጋቱ ጊዜያዊ ስለሆነ፣ ባለሥልጣኑ የሚሰጣቸውን ተጨማሪ መረጃዎች ተከታተሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

@etconp

Comments

Be the first to add a comment