👉ከልስን ፕላስተር ስራ በፊት የኮለመን መቆርቆር (Concrete Hacking) ጥቅም እና ጥንቃቄዎች!
🧐🏗️ ━━━━━━━━━━━━━
በምስሉ ላይ እንደምናየው የኮንክሪት ኮለሙ አካል በቺዝል/በመዶሻ ተቆርቁሯል (Hacking)። ይህ የሚደረገው የኮንክሪቱ ለስላሳ ገፅታ (Smooth Surface) ከፕላስተር ሞርታር ጋር በቂ ትስስር (Mechanical Key / Bond) እንዲኖረው ለማድረግ ነው።
🌟በ Concrete Hacking ወቅት ትኩረት የሚሹ ቁልፍ ነጥቦች፦
1. Density & Pattern: በቀጣይ የሚመረገው ፕላስተር እንዳይላጥ በየ 2.5cm - 5cm ርቀት በ m^2 ቢያንስ ከ 250 እስከ 300 የሚደርሱ ነጥቦች (Hacking Marks) መቆርቆር አለባቸው።
2. Proper Cleaning: ከተቆራቆራ በኋላ የቀረው አቧራ እና የኮንክሪት ብናኝ በውሃ በጥንቃቄ መፅዳት አለበት (አቧራ ካለ ሞርታሩ አይጣበቅም)።
3. Alternative Bonding Agents: በአሁኑ ጊዜ መቆርቆር በሚተኩ እንደ SBR / Chemical Bonding Agents እና Spatterdash Slurry (የሲሜንቶ እና አሸዋ ወፍራም እርጭት) መጠቀም የበለጠ ቀልጣፋና አስተማማኝ ውጤት ይሰጣል።
☄በእርስዎ ሳይት ላይ ለኮንክሪት እና ፕላስተር ትስስር Hacking ይመርጣሉ ወይስ Bonding Agent? ሃሳብዎን በኮሜንት ያካፍሉን!
👇
@etconp