👉በመርካቶ ከ200 በላይ ነጋዴዎች ሊነሱ ነው

🚧በአዲስ አበባ ከተማ እምብርት፣ መርካቶ አካባቢ ጣና የገበያ ማዕከል ፊት ለፊት የሚገኙ ከ200 በላይ ነጋዴዎች የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በ20 ቀናት ውስጥ የንግድ ቤቶቻቸውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።

💫የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 1 ጽህፈት ቤት ለተከራዮች ያሰራጨው ይፋዊ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ነጋዴዎቹ የንግድ ቤቶቻቸውን እንዲያስረክቡ የተጠየቁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚያካሂደው "የኮሪደር ልማት" ስራ ቦታው ተመርጦ እንዲለቀቅ በመጠየቁ ነው።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment