🍃🕯 ˓٭˛ ،
🌸🌹
እናንተ የጾመኞች ስብስብ ሆይ! ዛሬ ፀሐይ ስትጠልቅ ወደ ጁምዓህ ቀን እና ሌሊት ትገባላችሁ።
• በዚህም ወቅት እኛም ሆንን እናንተ በውዱ ነቢይ ሙሐመድ (
📿) ላይ ሰለዋት ማብዛት ይወደድልናል [ይኖርብናል] ።
• ከጨለማ ወደ ብርሃን እንዲያወጣን አላህ በላከው ነቢይ ላይ ሰለዋትና ሰላምታ አብዙ።
• ከእሳት አውጥቶ
ስፋቷ እንደ ሰማይና ምድር ወደሆነችው ጀነት መሪ በሆነን፣ ሱናው እዝነት በሆነልን፣ ልደቱ ለዘላለማዊው የኋለኛው ዓለም ሕይወት መዳኛና መሰላል በሆነልን ነቢይ ላይ ሰለዋት አውርዱ።
•
አላህ ሆይ! ሙአዚኑን ስንሰማና ለጥሪው ምላሽ ስንሰጥ፣ ነቢዩ ሙሐመድ (
📿) ከጌታቸው ብርሃን እንደወረደላቸው ስንመሰክር በነቢዩ ላይ ሰለዋት ይውረድ።
• ከጌታችሁ የአስር እጥፍ በረከትን በምትመኙት ልክ፣ በመመሪያው ብርሃንና በብሩህ መብራት በሆኑት ነቢይ ላይ ሰለዋትና ሰላምታ አውርዱ።
•
ነቢዩ (
📿) እንዳሉት "በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ፣ አላህ በእርሱ ላይ አስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል።"
•
ጌታ ሆይ! በውዱ ነቢይ ሙሐመድ (
📿) ላይ ሰለዋት የሚያወርዱት ሰዎች ባሉበት ልክ፣ ሰለዋትና ሰላምታ እንዲሁም በረከትን አውርድባቸው።
•
ጌታ ሆይ! ስለ ሰለዋት በዘነጉት ሰዎች ልክም፣ በሳቸው ላይ ሰለዋት፣ ሰላምታና በረከትን አውርድባቸው።
🔵 @TewhedandSuna 🌐