ጤና ይስጥልኝ!
በኢትጵያ የምርጫ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ላይ ስለተሰጡ አንዳንድ የቃል ወይም የቃላት ትርጓሜ እንደምናቀርብ በገለጽነው መሠረት የሚከተለውን አቀርባለሁ፡፡
መልካም ንባብ!
የውጭ የምርጫ ታዛቢ ማለት አገሪቱ በተቀበለቻቸው ስምምነቶች መሠረት በመንግስት ምርጫን እንዲታዘቡ የሚጋብዙ መንግስታት ወይም ዓለምአቀፍ አህጉራዊ፣ክፍለ አህጉራዊ ተቋማት እንዲሁም በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የምኒቀሳቀሱ መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ያሆኑ ድርጅቶች ናቸው፡፡
ተቀማጭ ወኪል ማለት በምርጫ ለመወዳደር በተመዘገበ የፖለቲካ ድርጅት ወይም የግል ዕጩ ተወክሎ በምርጫ ክልልና በምርጫ ጣቢያ በመቀመጥ የምርጫው ሂደቱንና የወካዩን መብት መከበር የሚከታተል ሰው ነው፡፡
ደረጀ ማርቆስ
መጋቢት 2013 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment