⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ሰበር ዜና¡~
•
ዓለም ሁሌም የምታወራው አዲስ ነገር አላት። ፖለቲካው፣ ትንታኔው፣ ወሬው... መቼም አያልቅም። ስልካችንን እና ቴሌቪዥናችንን ባበራን ቁጥር፣ ዓለም አሁን ካልሰማናት የምትፈርስ ይመስል በየደቂቃው በዜና ታጣድፈናለች።
• ግን እዚህ ግርግር ውስጥ ምን ያህል ውድ ጊዜያችንን እያቃጠልን እንደሆነ አላስተዋልንም። የሌሎችን "ሰበር ዜና" ለመስማት ስክሪን ላይ ስናፈጥ፣ የራሳችን ዕድሜ በዝምታ እያለቀ የራሱን የሞት "ሰበር ዜና" እያቀረበልን ነው።
•
ወዳጄ... አእምሮህን ከሚያደነቁረው ከዚህ ሁሉ ጫጫታ ራስህን አግልል። የልብህን እርጋታ ቀስ በቀስ ከሚሰርቀው የሚዲያ ሱስ ራቅና ስክሪንህን ዝጋው።
• ቁርኣንህን አንሳ። ጊዜው በፍጥነት እየሮጠ ነው። እነዚህ የተከበሩ የረመዷን ቀናት በቶሎ ያልፋሉ፤ ወይም ደግሞ ቀናቶቹ ሳያልቁ አንተ ታልፋለህ።ጊዜህን ተጠቀምበት፤ ቀናቶቹ የተቆጠሩ ናቸውና!
أياماً معدودات....
©abu sufyan
🔵 @TewhedandSuna 🌐
Wb