ስለስመዎት አስበው ያውቃሉ?
የፍትሀ ብሔር ህጋችን ስለስም ዘርዘር ያሉ ድንጋጌዎችን ይዟል። አንድ ሰው አንድ የቤተዘመድ እና የአባት ስም ሊኖረው፤ አንድ ወይ ሁለት የግል ስሞች ሊኖሩት እንደሚችል ደንግጓል። የግል ስም አሰጣጥን በሚከተለው መንገድ እንዲሆን ደንግጓል።
1. የአንድን ልጅ የግል ስም የሚመርጠው አባቱ ነው፡፡ አባቱ በሌለ ጊዜ የአባቱ ቤተዘመዶች ይመርጣሉ።
2. ለልጁ ሁለተኛ የግል ስም እናቱ ወይም እርሷ የሌለች እንደሆነ የእናቱ ቤተዘመዶች መርጠው ሊያወጡለት ይችላሉ።
3. የልጁ አባት ያልታወቀ በሆነ ጊዜ ወይም የልጁ አባት ወገን የሆኑ ቤተዘመዶች የሌሉት የሆነ እንደሆነ የልጁ እናት ወይም እርሷ ባትኖር የእናቱ ቤተዘመዶች ለልጁ ሁለት የግል ስም ሊሰጡት ይችላሉ።
4. ከላይ የተጠቀሱት ቤተሰቦች በሌሉበት ወቅት ለልጁ በጣም ቅርብ የሆነ ወደ ላይ የሚቆጠር ወላጅ ወይም የጎን ዝምድና ያለው ሰው የቤተዘመድ እንደራሴ በመሆን የግል ስም ሊያወጡለት ይችላሉ፡፡ በአጋጣሚም በቤተዘመድ እንደራሴዎች እንደራ በመሆን የዝምድና ደረጃ እኩል በሚሆኑበት ጊዜ የልጁን የግል ስም የሚመርጠው በእድሜ ከፍ ያለው ወደላይ የሚቆጠር ወይም የጎን ዝምድና ያለው ሊሆን ይችላል።
5. በመጨረሻም ከላይ የተጠቀሱ ሰዎች በሙሉ የሌሉ እንደሆነ የልጁን የግል ስም የሚያወጣው የክብር መዝገብ ሹም መኮንን በአካባቢው ከሚገኙ ልማዳዊ ስሞች መካከል መርጦ ይሆናል።
ይህንን ካነበቡ በኋላ የርሰዎ ስም እንዴት እንደወጣና ህጉንስ እንዴት እንደተመለከቱት አስተያየተዎትን እንዲሰጡን በክብር ጋብዘነዎታል።
እነዚህና መሰል የህግ ግንዛቢያችንን የሚጨምሩ ጉዳዮችን፣ አዳዲስ የሚወጡ ህጎችን፣ አዳዲስ ህግ-ነክ መረጃዎችን ለማግኘትና ለየትኛውም የህግ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን
https://t.me/getuasnakew ሳብስክራይብ የቴሌግራም ግሩፓችንን
https://t.me/debgzv174 ደግሞ ጆይን ያድርጉ።
አስተማሪ መልእክቶቻችንን ሼር በማድረግና የቴሌግራም ግሩፓችንንና ቻናላችንን ደግሞ ተደራሽ እንዲሆን ጓደኞቻችሁን አድ በማድረግና በመጋበዝ አጋርነተዎን ያሳዩን፤ ያበረታቱን።
በስልክ ልታገኙን የምትፈልጉ ወዳጆቻችን 0913771324 ላይ መደወል ይቻላል።
ምርጫዎት በአካል ቢሮ መምጣት ከሆነ ደግሞ መገናኛ የካ ክ/ከተማ አጠገብ ከሚገኘው ሰላም ታወር ጀርባ የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፊትለፊት እንገኛለን።