የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚወሰኑ ፍቺ እና ጉድፈቻ ውሳኔዎች በፍርድ ቤቶች ምዝገባው ነገ ይጀምራል፡፡
**********************************************
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሚመዘግባቸው ኩነቶች መካከል በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚሰጥባቸው ጉድፍቻ እና ፍቺ በፍርድ ቤቶቹ ከነገ ጀምሮ መመዝገብ ይጀምራል፡፡
ሁለቱ ተቋማት የኩነት ምዝገባን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡
ይህንን ተከትሎ በወሳኝ ኩነት ፅንሰ ሀሳብ እና የምዝገባ ስርዓት በሚመለከት በከተማዋ ለሚገኙ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመራሮች፣11 ምድብ ችሎት የቤተሰብ እና የጉዲፈቻ ችሎት ዳኞች፣ችሎት አስተባባሪ ሪጅስትራሮች፣ፍርድ ቤቶቹ የሚገኙበት የወረዳ ስራ አስፈፃሚ እና የወረዳው የሲቪል ምዝገባ ስራ አስኪያጅ በተገኙበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡
ስለሆነም በነገው ዕለት ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በአራዳ እና ቦሌ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎቶች የፌደራልና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሶር አምባ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው በአራዳ ምድብ ችሎት ከጥዋቱ በ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ምዝገባው በይፋ ይጀመራል፡፡
Comments
Be the first to add a comment