👉የኮሪደር ስራን የሚቆጣጠር መስሪያ ቤት ተቋቋመ

🚧የአዲስ አበባን የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች እና የኮሪደር ስራን የሚቆጣጠርና የሚመራ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ተቋቋመለት፡፡

የተቋቋመው መስሪያ ቤት እስካሁን የተሰሩና ከዚህ በውሃላም የሚሰሩ የወንዝ ዳርና የኮሪደር ልማት ስራዎችን የሚመራና የሚቆጣጠር ነው ተብሏል።

በዚህም የኮሪደርና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች መቆጣጠርና ማስተዳደር ባለስልጣን ተቋም በከተማ አስተዳደሩ ተሰምቷል።

ለአዲስ አበባ የመጀመሪያው የሆነውና በግንባታ ላይ ያለው ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ መናፈሻ የሚደርሰው የ21.5 ኪ.ሜ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት ስራ 90 በመቶ መድረሱን የከተማዋ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስፈፃሚና የ የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ኮሪደር ልማት ምክትል አስተባባሪ አቶ ዋለልኝ ደሳለኝ ተናግረዋል።

በተጨማሪም እስከ መጪው ጥቅምት ወር መጨረሻም አጠቃላይ ስራው ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

ከዚህ በኋላም ስራውን የሚቆጣጠርና የሚከታተል ተቋም መቋቋሙን ተከትሎም የወንዝ ዳር ፕሮጀክቱ ያለምንም መቆራረጥ በቋሚነት የሚሰራ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

Via ሸገር ሬድዮ

@etconp

1 comment

ተጠሪነቱ ለማን ነው? የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ማስተዳደር አይችልም? የመንግስት ወጪን ማብዛት ነው ብዬ አስባለሁ።