ተስፋ (Expectation)

በሰዎች ላይ የምታደርገው ተስፋ በጨመረ መጠን፣ ሳያስቡት በሕይወትህ ላይ የሚኖራቸው ተፅዕኖ ይጨምራል። ቃል ይገባሉ፣ እድሎችን ያቀርባሉ። አንተም ቃላቸውን አምነህ እቅድህን ትቀይራለህ፣ ሌሎች እድሎችን ትተዋለህ፣ የወደፊት ዕቅድህንም በቃላቸው ላይ ትገነባለህ።

ከዚያ ግን ሕይወት ይቀየራል። ይረሳሉ ወይም ሁኔታቸው በቅፅበት ይለወጣል። እነሱ ሕይወታቸውን ሲቀጥሉ፤ አንተ ግን ባልተፈጸሙ ተስፋዎች ላይ የተገነቡ ዕቅዶችህን ዋጋ ትከፍላለህ።

ይህ በሥራ ዓለም ብቻ የሚከሰት አይደለም። በወዳጅነት፣ በቤተሰብ፣ በአብዛኛው ማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ ይከሰታል። "ይመጣል" ብለህ የጠበቅኸው ሰው ላይመጣ፤ "ከጎኔ ይቆማል" ብለህ ያሰብከው ሰው ሊሄድ፤ በጣም ያመንከው ሰውም ሊለወጥ ይችላል። እንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች የሰው ተፈጥሮ አካል ናቸው።

እውነተኛው የሕመም ምንጭ ግን የእነሱ ድርጊት ብቻ አይደለም። ሰላምህ ሙሉ ለሙሉ ሰዎች ቃላቸውን በመጠበቃቸው ላይ ከተመሠረተ፣ እያንዳንዱ የተሰበረ ቃል ያናውጥሃል። ነገር ግን ልብህ በአላህ ላይ ብቻ ከተደገፈ፣ የሰዎች ቃል መሠረት ሳይሆን ተጨማሪ ፀጋ ይሆናል።

ቃላቸውን ከፈፀሙ አልሐምዱሊላህ፤ ካልፈፀሙም አቅጣጫህ፣ ሰላምህና ቁርጠኝነትህ አይለወጥም፤ ምክንያቱም ጉዞህን ከመጀመሪያው በሰዎች ላይ ሳይሆን በአላህ ላይ መሥርተሃልና።

"የሰዎች ቃል እንደ አንድ ሊፈፀም የሚችል እድል እንጂ እንደ መሠረት ሊቆጠር አይገባም። ብቸኛው የማይናወጥ ቃል የአላህ እና ለአላህ ተብሎ የተገባ ነው።"

© Huneynn

🌱 @TewhedandSuna

Comments

Be the first to add a comment