የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ሰላም!
በ የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ ቁጥር 1100/2011 አንቀጽ 20 መሠረት የግዴታ አገልግሎትን በተመለከተ ማንኛውም የሠራዊት አባል ልዩ ሥልጠና ወይም ትምህርት ተከታትሎ ከጨረሰ በኋላ በስልጠና ወይም በትምህርት የቆየበትን ጊዜ እጥፍ የማገልገል ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም ከሙያዎቹ ልዩ ባህሪና ከሚያስከትሉት ከፍተኛ ወጪ አኳያ የስፔሻሊሰት ሐኪም፣ አብራሪ፣ አነስተቲስት፣ ራዲዮሎጂሰት፣ ሰርጀን፣ የአውሮፕላን ወይም ስትራቴጂክ መሳሪያዎች ቴክኒሽያን፣ የባህር ኃይል፣የስፔስ እና የሳይበር ሙያተኛ፣ልዩ ኃይል፣ እና አየር ወለድ የአገልግሎት ውል ግዴታው ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰን ይሆናል፡፡
ሰናይ አርብ! (9/04/2013 ዓ.ም)(ኦምኒኤል)
Comments
Be the first to add a comment