🏗️ ውጤታማ የቁጥጥር ሥርዓት፤ ለኮንስትራክሽን ዘርፍ ተወዳዳሪነት!

የኮንስትራክሽን ዘርፍ ለሀገራዊ ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ብልፅግና ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ይሁን እንጂ ዘርፉ በጠንካራ፣ ውጤታማና ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓት ካልተመራ ለሰው ሕይወት፣ ለአካባቢ፣ ለንብረትና ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ስጋት ሊሆን ይችላል።

🔹 የቁጥጥር ሥርዓት ለምን ያስፈልጋል?

በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ የሕግ ተገዥነት፣ የግንባታ ኮዶች፣ የቴክኒክ ደረጃዎችና የሙያ ሥነ-ምግባር በተገቢው መንገድ ካልተተገበሩ የግንባታ ጥራት መጓደል፣ የሥራ ቦታ አደጋዎች፣ የሀብት ብክነትና የፕሮጀክት መጓተት ያጋጥማሉ።

ይህም ከቀጥተኛ ጉዳቶች ባሻገር

▪️ ተጨማሪ የግንባታ ወጪን ያስከትላል።
▪️ የፕሮጀክት ጊዜን ያራዝማል ▪️ ለኢንሹራንስና ለጥገና ወጪዎች መጨመር ምክንያት ይሆናል
▪️ የሙያተኞችን የሥነ-ልቦና ደህንነት ይጎዳል
▪️ የዘርፉን ገጽታና ተወዳዳሪነት ያዳክማል

🔹 ውጤታማ ቁጥጥር ምንን ያረጋግጣል?

የኮንስትራክሽን ቁጥጥር ሥርዓት የግንባታ ግብዓቶችን፣ የሥራ ሂደቶችንና የፕሮጀክት ዑደትን በሙሉ የሚሸፍን ነው።

ከፕሮጀክት ጥንስስና ዲዛይን ጀምሮ፣ በዕቅድ፣ በአስተዳደርና በግንባታ ትግበራ እስከ ማፍረስና መልሶ ግንባታ ድረስ የሚዘልቅ ሂደት ነው።

🌟በዚህም

✅ የግንባታ ጥራትና ደህንነት ይረጋገጣል።
✅ የሕግ፣ የደንብና የቴክኒክ ደረጃዎች ተፈፃሚነት ይጠናከራል።
✅ የሰው ሕይወት፣ የሠራተኞችና የሕዝብ ደህንነት ይጠበቃል።
✅ የአካባቢና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ይረጋገጣል።
✅ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ፣ በበጀትና በተፈለገው ጥራት እንዲጠናቀቁ ያግዛል።

🔹 የባለድርሻ አካላት ኃላፊነት

የመንግሥት ተቋማት፣ ባለሙያዎች፣ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች፣ ገንቢዎችና ሌሎች የዘርፉ ተዋናዮች የግንባታ ሕጎችን፣ ደንቦችን፣ ኮዶችን፣ የቴክኒክ ደረጃዎችን፣ የሥራ ቦታ ደህንነትና የአካባቢ ጥበቃ መስፈርቶችን ማክበር አለባቸው።

ይህ የአንድ ተቋም ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የመላው የኮንስትራክሽን ዘርፍ ተዋናዮች የጋራ ግዴታ ነው።

🏗️ ግንባታ ሀገር ነው!

የተገነቡ መሠረተ ልማቶች የዛሬን ትውልድ ብቻ ሳይሆን የነገውንም ትውልድ የሚያገለግሉ የሀገር ሀብቶች ናቸው። ስለዚህ ጥራታቸውን የጠበቁ፣ ደህንነታቸው የተረጋገጠና በሕግ መሠረት የተገነቡ ፕሮጀክቶችን ማስፈፀም የሀገር ልማትና ብልፅግና መሠረት ነው።

ውጤታማ የቁጥጥር ሥርዓት የግንባታ ጥራት መሠረት፣ የሕዝብ ደህንነት ዋስትናና የሀገራዊ ተወዳዳሪነት መሠረተ ልማት ነው!

Via የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን

@etconp

Comments

Be the first to add a comment