👉በመንግሥት የቤት ልማት መርሃ ግብር ተመዝግበው ከጉሮሯቸው እየቀነሱ በባንክ ሲቆጥቡ የቆዩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ ከ14 እስከ 20 ዓመታት የዘለቀው ጥበቃቸው ዛሬ ድረስ ምላሽ ባለማግኘቱ በቤት ኪራይ የተሰቃዩ እንደሚገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ገልጸዋል።

🏛የኑሮ ውድነቱ እንዲሁም ቤት የኪራይ ጭማሪ እጅጉን የተጫናቸውና ፈተና የሆነባቸው ቆጣቢዎች፣ ለዓመታት ያሳዩት ትዕግሥትና የከፈሉት መስዋዕትነት ከግምት ገብቶ የከተማ አስተዳደሩ ግልጽና ተጠያቂነት ያለበት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጣቸው " ድምጻችን ይሰማ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

"ሰው ሊሞት ሲል ነወይ ማረፊያ የሚሰጠው ?" ሲሉ የጠየቁት ቆጣቢዎቹ ከዚህ ቀደም የተገቡ ቃልኪዳኖች እንዲጠበቁ፣ ከምንም በላይ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ቤት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

Via TikVah Ethiopia

@etconp

Comments

Be the first to add a comment